‹‹ቤተሰቦቼ አሸባሪ ተብለው ቤት የሚያከራያቸው አጥተዋል፤ ልጆቼ በረንዳ ላይ ወድቀዋል፤ ቤተሰባችን ተበትኗል››
ም/ኢንስፔክተር ሙልዬ ማናዬ ረታ (7ኛ ተከሳሽ)
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) ዋስ እንዲሆኑ ለዛሬ ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የደረሰው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡
ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ፅጌና ፋሲል የኔዓለም እንዲሁም ከሌሎቹ የአሸባሪው ድርጅት አመራሮች ጋር በአካልና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች በመገናኘት ስለ ሽብር ተግባሩ አፈፃፀም በመግባባት፣ ኤርትራ ወደሚገኘው የግንቦት ሰባት ካምፕ ሄደው ስልጠና በመውሰድ፣ ተልዕኮ ተቀብሎ ወደ ሀገር ውስት በመመለስ፣ ….›› የሚል ክስ ስለመሰረተባቸው ነው፡፡
የልደታ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለሚገኙት ተከሳሾች ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት እንዲሰጡ ወስኖ የነበር ቢሆንም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት…
View original post 300 more words
Discussion
No comments yet.