የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግሬስ ፓርቲ መሪ ኦቦ በቀለ ነጋ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገው የእጅ ስልካቸውን ተነጥቀዋል ።በቀለ በኃይል ወደመኪናቸው ያስገቧቸው ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች እንደደበደቧቸውም ከዚህ በታች በምታነቡት ደብዳቤያቸው ይፋ አድርገዋል ።
=========
ወዳጆቼ
ዛሬ ማለዳ ወደ ስራ እያመራሁ ሲቪል የለበሱ 4 ሰዎች ስሜን ጠርተው ሰላምታ ካቀረቡልኝ በኋላ ፖሊሶች መሆናቸውን ነግረውኝ እኔን ካስቆሙበት ቦታ አጠገብ ወደሚገኘው መኪናቸው እንድገባ ጠየቁኝ።ፈቃደኛ አለመሆኔን ስነግራቸውም እጆቼን ይዘው እየጎተቱኝ በመኪናቸው የኋላ መቀመጫ ላይ እንድቀመጥ አድርገውኝ መንዳት ጀመሩ ።
መኪናው መንቀሳቀስ እንደጀመረም መማታት ጀመሩ ፣በቀኝና በግራዬ የተቀመጡት ሁለት ሰዎች ሲደበድቡኝ ጋቢና የተቀመጠው ወደኋላ ዞሮ በመሳሪያው ፊቴን ይነካ ነበር ።
እየደበደቡኝ ይህንን የሚያደርጉት ማስጠንቀቂያቸውን ችላ ብዬ ለሚዲያ መረጃ በመስጠቴ እንደሆነ ይነግሩኝ ነበር ።ድብደባቸውን እንዳቆሙም መሳሪቸውን እንደደገኑ ስልኬን ወሰዱብኝ ።የሚሉኝን ካላደረግኩም ለእኔና ለቤተሰቦቼ እንደሚመጡ አስፈራርተውኛል።
“ከዛሬ ጀምሮ ከቤትህ ብትወጣ ወይ ሚዲያ ብታናግር በአንተም ሆነ በቤተሰቦችህ ላይ ለሚሆነው ነገር ሃላፊነቱ ያንተ ነው” ብለውኛል ።
የእኔ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቼ ህይወት አደጋ ውስጥ እንደሆነ በመንገርም ከመልቀቃቸው በፊት የሚሉኝን ካላደረኩ እንደሚገሉኝ ዝተውብኛል።
“ከእንግዲህ ወዲህ…
View original post 115 more words
Discussion
No comments yet.