![የመጀመርያ ደረጃ አስተማሪ የለቅሶ ሥነ-ሥርአት በተደረገበት ጊዜ የተገኘ ለቀስተኛ በሆሎንኮሚ ከተማ(Holonkom)እአአ 2015[ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]](https://i0.wp.com/gdb.voanews.com/6E355E87-6213-439B-984A-5F4F492F25AF_cx0_cy8_cw0_w1000_r1_s_r1.jpg)
የመጀመርያ ደረጃ አስተማሪ የለቅሶ ሥነ-ሥርአት በተደረገበት ጊዜ የተገኘ ለቀስተኛ በሆሎንኮሚ ከተማ(Holonkom)እአአ 2015[ፋይል ፎቶ – ሮይተርስ/ REUTERS]
በአዲስ አበባና ፊኒፊኔ ዙሪያዋ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለዉ ንድፍ ገበሬዎችን ያፈናቅላል ቋንቋና ባህል ያጠፋል በሚል በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄደዉ ተቃዉሞ የታሰሩት ይፈቱ የሚለዉን መፈክር ጨምሮ ዛሬም በአንዳንድ ስፍራዎች ቀጥሏል።
“ተማሪዎችን ሳይሆን የቀን ሰራተኞን መደብደብ ጀመሩ፣ እነርሱም በመደብደባቸዉ ተቆጥተዉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በመቀላቀል በሰልፉ ተካፈሉ” ብለዋል።
በተጨማሪም የወረዳዋ ፓሊሶችና ካቢኔ አባላት ተኩስ ከፍተዉብን እኛም ድንጋይ ወርዉረን ተከላክለና ብሏል ተማሪዉ፣ ተከሰተ የተባለዉን የተቃዉሞ ስፍና ጉዳት አስመልክቶ የመሰላ ከተማ ወረዳ አስተዳዳሪና ደህነት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዲኔ አህመድን እንዲሁም የምእራብ ሀረርጌሬ ዞን አድተዳዳሪ አቶ አልዩ ኡመሬን በወረዳዉ የኦህዴድ ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሙክታርን ለማነጋገር የደረገነዉ ሙከራ ስልካቸዉ ስለማይነሳ አልተሳካም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት በአዳማ ዩኒቬርሲቲ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በተካሄደ ተቃዉሞ ሁለት ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች መገደላቸዉ ታዉቋል።
አዳማ ዩኒቬርሲቲ
አንደኛዉ ተማሪ ወዲያ ሲሞት የሁለተኛዉ ሕይወት ያለፈዉ ዛሬ መሆኑን ጥቃት እንዳይደርስበት በመስጋት ስሙን እንዳይጠቀስ የጠየቀ ተማሪ ገልጾልናል።
“ተማሪዉ በዩኒቬርሲቲዉ ቅጥር ግቢ ፍርሃት እንደነገና ለራሱም ሕይወት እንደሚሰጋ ጨምሮ ገልጾልናል” በለዋል።
ትላንት በፊዴራል ፖሊሶች ተገደሉ ሰልተባሉ ተማሪዎች ለማጣራት ወደ አዳማ ፒሊስ ጣቢያ ስልክ ደዉለን ፒሊስ ደረጀ አድነዉን አግኝተናል።
“አዎ የዚህ መስሪያ ቤት አባል ነኝ ፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የተጣራ መረጃ የለኝም ፥ ጥዋት በዩኒቬርሲቲዉ ትንሽ ረብሻ እንደነበረ ስምቻለሁ በተረፈ ሰላም ነዉ” ብሏል።
በዩኒቨርስቲዉ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ እንዲያስረዱም ወደ አዳማ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ለሚ ጉታ ቢሮም ስልክ ደዉለን ነበር ስልካቸዉ አያነሳም።
በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ከተማ የመሰናዶና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ጥቁር ስልብ ለብሰዉ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ተቃዉሞና መፈክሮቻቸዉን አሰምተዉ እንደተመለሱ ከስፍራዉ ያነጋገርናቸዉ የዓይን እማኝ ገልጸዉልናል።
“ከጊዳ አያና ከተማ ካሁን በፊት ቁጥጥር ስር የዋሉ ከፊል ተማሪዎች መፈታታቸዉንና ሌሎች ግን አሁንም ታስረዉ እንደሚገኙ እኚሁ የዓይ እማኝ ገልጸዉልናል። በምስራቅ ወለጋ የጊዳ አያና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማረጋ ቀነዓ ስልካቸዉን አያነሱም። የወረዳዉ የትምህት ቢሮ ሃላፊ አቶ አዳነ አላምረዉ ስልኩን አንስተዉ ባልደረባችን ነሞ ዳንዲ ሊያነጋግር እራሱን ሲያስተዋዉቅ ስልኩን ዘግተዉታል” ብለዋል።
የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ክፍል ባለደረባችን ነሞ ዳንዲ ወደ ከተሞቹ ስልክ በመደወል ያጠናቀረዉን ዘገባ ትዝታ በላቸዉ አቅርባዋለች። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Discussion
No comments yet.