Uncategorized

የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጠንካራ የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ – አለማየሁ አንበሴ

 • የእርዳታ አሰጣጥ የተጠና እንዲሆን ጠይቋል
  –    ህብረቱ የ25 ሚ.ዩሮ እርዳታ ሰጥቷል ተብሏል
  በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች በተለይም ከአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተቃውሞ የደረሰው ሞትና የሰብአዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራና የሰብአዊ መብት ባለሙያዎችና የተባበሩት መንግሥታት ምርመራ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ቀረበ፡፡ ለአገሪቱ የሚደረገው እርዳታም የተጠና እንዲሆን ተጠይቋል፡፡
  በኦሮሚያ ክልል ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ተቃውሞና ግጭት ለሁለት ወራት መዝለቁን የጠቆመው የውሣኔ ሃሳቡ፤ በግጭቱ 140 ሰዎች መገደላቸውንና የተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች ፣ ተማሪዎች፣ ምሁራን፣ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መታሰራቸውን በመጥቀስ እየተፈፀሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሣሣቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጿል፡፡
  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፤ በፖሊሶች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ እስካሁን ያሉበት አይታወቅም ያለው የውሳኔ ሃሳብ፤ የሲፒጄን ሪፖርት ጠቅሶ 17 ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙና 57 የሚዲያ ባለሙያዎችም ባለፉት 5 ዓመታት ሀገር ጥለው መሰደዳቸውን አመልክቷል፡፡
  ለፓርላማው የቀረበው በርካታ ነጥቦችን የያዘው ውሳኔ ሃሳብ፤ ከተቃውሞው ጋር ተያይዞ ተፈጽመዋል ያላቸውን የሞት፣ የእስራትና የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተግባራት በዝርዝር የጠቀሰ ሲሆን ተቃውሞውን ያሰሙ የህብረተሰብ ክፍሎች “ሽብርተኛ” መባላቸውን አውስቷል፡፡
  ተቃውሞውን ለማርገብ በመንግስት የፀጥታ ሃይል የተወሰደውን እርምጃ፣ በግጭት መሃል የተገደሉ 140 ዜጐችን ጉዳይና ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል ተጣርተው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቀው የውሳኔ ሀሳብ፤ መንግስት ማስተር ፕላኑን  መሰረዙን በበጐ እንደሚቀበለው አስታውቆ፣ በቀጣይ በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ መንግስትና ተቃዋሚ  ፓርቲዎችን ጨምሮ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ የህብረቱ ፓርላማ ጥሪ ያቀርብ ብሏል፡፡
  የውሳኔ ሀሳቡ የኢትዮጵያ መንግስት፤ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ስምምነቶችን እንዲያከብርና የዜጐችን በሠላማዊ መንገድ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብት እንዲያከብር እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መርማሪና የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ወደ አገሪቱ መጥተው ጉዳዩን በመመርመር  ሪፖርት ያቀርቡ ዘንድ መንግስት እንዲፈቅድ ይላል፡፡
  መንግስት ሚዲያዎችን ከማፈንና ከማዋከብ እንዲቆጠብ፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ስራቸውን በነፃነት እንዲሠሩ እንዲፈቅድና የመረጃ እቀባ ከማድረግ መንግስት እንዲቆጠብ ህብረቱ ጥሪ እንዲያቀርብም በውሳኔ ሃሳቡ ጠቁሟል፡፡
  ለሀገሪቱ የሚሠጠው እርዳታም ሆነ የልማት ድጋፍ በሀገሪቱ ለሚፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ግብአት አለመሆናቸውን፤  በተለይም አርሶአደሮችና አርብቶ አደሮችን እንደማያፈናቅል ማረጋገጥ ያሻል ያለው የውሳኔ ሀሳቡ፤ በአውሮፓ ህብረት የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍም የሰብአዊ መብት አጠባበቅን መሠረት ያደረገና የኢትዮጵያ መንግስት ዲሞክራሲን ለማስፋፋት ባከናወነው ተግባር ልክ መሆን እንዳለበት ጠቁሟል፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊ የነበሩትና ከዓመት በፊት ከየመን ተይዘው በኢትዮጵያ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚነገርላቸው እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፤ በአስቸኳይ ይለቀቁ ሲልም ጥያቄ አቅርቧል፡፡
  በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ታሪክ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበና ጠንካራ ጉዳዮችን ያካተተ ነው፡፡ በተባለው በዚህ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የፓርላማው አባላት በቅርቡ ድምፅ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የበጎ አድራጎት ሥራዎች የ25 ሚ. ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ህብረቱ ለኢትዮጵያ በአማካይ በአመት የ4 ቢሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይየሚታወቅ ሲሆን ከአሜሪካና ከእንግሊዝ በመቀጠል ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ተጠቃሽ ነው፡፡

ምንጭ – አዲስ አድማስ

Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Blog Stats

 • 52,293 hits
Advertisements
%d bloggers like this: