Archive for

በዳባት የሕዝብ ቁጣ አይሏል – የወያኔ ሥርዓት በቃን፤ ወልቃይት ወደ ቀድሞ ማንነቱ ይመለስ እያሉ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ዳባት የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ:: ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት መንገድ የዘጋጉት የአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄያቸው የወያኔ መንግስት በቃን ወደሚል ተሸጋግሯል:: ከወልቃይትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳው በዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሕዝቡ ያሳየው እምቢተኝነት ተጠናክሮ አሁን ጥያቄው ስር ዓቱ ይውረድ; የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች ወደ ቀድሞው ማንነታቸው ይመለሱ የሚል ሆኗል:: በተለይ ሕዝቡ እያሰማ … Continue reading

Breaking: በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ዙሪያውን በእሳት እየነደደ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካሞፓስ ዛሬ ማምሻውን የ እሳት ቃጠሎ ተነስቶ በወሊሶ ካምፓስ በ እሳት እየነደደ መሆኑ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አስታወቀ:: እንደመረጃው ከሆነ በወሊሶ ካምፓስ የተነሳው የ እሳት ቃጠሎን ማን እንዳስነሳውና እንዴት እንደተነሳ ለጊዜው ባይታወቅም እስካሁን የተማሪዎች መኝታ ቤት እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት እንዳልደረሰ የአይን እማኞች ገልጸዋል:: የአካባቢው ነዋሪዎች እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ ይገኛሉ::

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር ተከሰቷል

በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ ሹፌሮች የወያኔ አገዛዝ ያወጣውን የትራንስፖርት እና መንጃ ፍቃድ ሕግ በመቃወም የጠሩት የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት የአዲስ አበባን መንገዶች ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ውጪ በማድረጋቸው ተገልጋዩ በትራትስፖርት ችግር ሲገጥመው ተስተውሏል:: የአዲስ አበባን የታክሲ ሹፌሮች ከስራ ውጪ ለማድረግ እና ስራ ፈት ዜጎችን ለመፍጠር ታስቦ በወያኔ የወጣው አዲስ ሕግ ማንኛውም ሹፌር 21 ጊዜ ጥፋት … Continue reading

የፌደራል ፖሊስ ኢንስፔክተር ተስፉ በርካታ አባላቱን ይዞ ስርዓቱን ከዳ

(ዘ-ሐበሻ) የኢሕ አዴግ አስተዳደር ኢንስፔክተር ተስፉ የተሰኘ የፌደራል ፖሊስ ጦር መሪ በርካታ አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዞ ከሁመራ ስርዓቱን መክዳቱን የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ዘገበ:: እንደራድዮው ዘገባ ኢንስፔክተር ተስፉ ሁመራ እና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው ፌደራል ፖሊስ መሪ፣ ለህወሓት ታማኝ እና ጠንካራ ከሚባሉት ቀዳሚው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የካቲት 19 2008 ዓ.ም የሚመራቸውን በርካታ አባላት ከነሙሉ ትጠቃቸው ይዞ … Continue reading

በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ | ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ መንገዶች ተዘጋግተዋል

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀስቀሱን ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች አስታወቁ:: ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚገልጹት ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ ወይም ከዚያ ወደ ዳባት የሚያመጡ መንገዶች ተቃውሞውን ባነሳው ሕዝብ በድንጋይ እና በ እንጨት መዘጋጋቱ ተሰምቷል:: በዳባት ከተማ ሕዝቡ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያነሳው ከወልቃይት መሬት እና ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ እንደሆነ ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመው ሕዝባዊ ቁጣው እስከ እኩለሊት … Continue reading

ከሕይወት ሞትን ለምን? ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2008 ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ አእምሮ ያለው ያስባል፤ ልብ ያለው ስሜቱ ይነካል፤ ዓይን ካላየ፣ ጆሮ ካልሰማ፣ አእምሮ ካላሰበ፣ ልብ ካልተሰማው ሰውን ሰው የሚያደርገው ምንድን ነው? የትናንቱ ችግር መልኩን ለውጦ ሲመጣ፣ ትናንት ተሞክሮ ያልተሳካው የሕገ አራዊት መፍትሔ ዛሬ ዘመን ከተለወጠ በኋላ ይሠራል ብሎ መወራጨት ጥፋት ነው፤ ዓይን እያለ አለማየት ነው፤ ጆሮ እያለ አለመስማት … Continue reading

እኔና ሀያሲዎቼ! Bewketu Seyoum

(ቁጥር 1) ከአሜን ባሻገር በተባለው መጽሐፌ በላስታ የሚገኙትን የሮሀን ውቅር መቅደሶች ጎብኝቼ የተሰማኝን አድናቆት ጽፌ ነበር፡፡ መጣጥፌን የጀመርኩት እንዲህ በማለት ነው፤ ” የላሊበላ ኣዳራሾችን በቃላት ወይም በፊልም ለማስረዳት መሞከር አሪፍ ቅኔን በዱዳ ቋንቋ ለማስረዳት እንደመሞከር ነው፡፡ የላሊበላን አዳራሾች ምን ብለን እንጥራቸው?ካንድ ዐለት የተፈለፈሉ መቅደሶች የሚለው አገላለጽ ያንስባቸዋል፡፡“ ይህ የአድናቆት አገላለጽ እንደ ነውር ተቆጥሮ ያነቅፈኛል ብየ … Continue reading

የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን (ህወሃት) በሰሜኑ በኩል የሚደያረገዉ ዉጊያና ሰራዊቱ

ልኡል አለም መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል። ኤርትራ ለዘመናት የደከምንበትን እና ያጎለበትነዉን ሐገራዊ እድገት ለመቀልበስ አሸባሪዎችን አሰልጥና ወደ ሐገራችን እየላከች አርበኞች ግንቦት 7 በተባለ የሻቢያ ሐይል እየተመታን እንገኛለን በመሆኑም ከኤርትራ ድንበር ዉጭ በገዛ መሬታችን ላይ ገዢ ቦታዎችን … Continue reading

Breaking: የቴዲ አፍሮ የአዲስ አበባ ኮንሰርት ተከለከለ – ለምን? ዝርዝር አለን

(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን ቅዳሜ ማርች 5, 2016 በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል ሊደረግ የነበረው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ተከለከለ፡፡ በመላው ኦሮሚያ እንዲሁም በአማራው ክልል በተለይም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ውስጥ ውጥረት ውስጥ የገባው ኢሕ አዴግ መንግስት ጦሩን ወደ ኤርትራ ድንበር ካስጠጋና እንደዚሁም ደግሞ በኦሮሚያ በ8 ዞኖች ከፋፍሎ ወታደራዊ አስተዳደር ካወጀ በኋላ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሕዝብ አመጽ ይነሳል በሚል … Continue reading

የሕወሓት ጦር ኦሮሚያን በ8 ቀጠናዎች ከፋፍሎ በሕዝቡ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑ ተጋለጠ

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቃሴ 4ኛ ወራት እያስቆጠረ ነው:: ቀደም ሲል የኦሮሞ ሕዝብ ቁጣ እየተቀጣጠለ ሲሄድ ክልሎ ከኦህዴድ አስተዳደር እጅ ወጥቶ በቀጥታ በሕወሓት መሪዎች; የደህነነት ኃይሎች እና ወታደሮች እንዲመራ መደረጉን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ስትዘግብ ነበር:: ሕወሓት ክልሉን በደህንነት እና በወታደሮች እንዲመራ ቢያደርግም ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳይመጣ ይበልጡኑ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ከማስተር ፕላኑ አልፎ ወደ ሰብ አዊ መብቶች … Continue reading

ሕዝቦቹን ተዉና ፖለቲከኞቹን ስቀሏቸው ! ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

አንድ ብሔር የቱንም ያህል ሰፊ ቁጥር ቢኖረው ለእኔ ያንሰኛል ። የእኔ የምለወረን ብሔር ነጥዬ ማሞገስ የራስን መውደድ ሳይሆን የሌላውን ማሳነስ ፣ ለራስም ማነስ ይሆናል ። ለአንድ ብሔር ነጥሎ የሚሟገት ሰው ለእኔ የተማረ እንጂ አዋቂ ሊባል አይችልም ። ትምህርት እንጂ እውቀት መጥበብን አያመጣም ። ከይትኛውም ብሔር ሳይሆን ከተበዳዮች ጎን እቆማለሁ ። ኢትዮጵያ ውስጥ በብሔር ደረጃ ተጨቋኝ … Continue reading

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ የአማራ ማንነት ድራማ በመስራት አይፋቅም!!!

ከታደሰ ዶሰኛው የወልቃይት ጠገዴን ጠለምት የአማራ ማንነት ማክበር ሲገባው መሬቱን ለመንጠቅ ሲል ለማጭበርበር ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የመጣቸውን ካድሬዎችና ተከዜን አሻግሮ በአማራው ላይ ያሰፈራቸውን መጤ ትግሬዎች ይዞ በአማራው ሀገር ጎዳና የወጣው ህወሀት በወልቃይ ጠገዴ አማራ ህዝብ ላይ ያለውን ንቀት አሳይትዋል።በማፈን፣በማሰር፣በመግደልና በማጭበርበር የአንድን ህዝብ ማንነት መፋቅ እንደማይቻል በዚህ አሳፋሪ ተግባሩ አስመስክርዋል፣የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ የአማራ ማንነት ድራማ በመስራት … Continue reading

የገዳ አባቶች መግለጫ አወጡ – “የኦሮሞ ህዝብ እንኳን የሚወደው ልጁን ገድለውበት ይቅርና የሚወደውን ከብቱን ሲነኩበት አይወድም”

አባ ገዳዎች ዛሬም ዳግም ወደ ሞራል ማማ ተምዘገዘጉ!!! ዳንኤል ፈይሳ እንደዘገበው ”የኦሮሞ ህዝብ እንኳን የሚወደው ልጁን ገድለውበት ይቅርና የሚወደውን ከብቱን ሲነኩበት አይወድም።በገዳ ሥርዓት አንድን የኦሮሞ ልጅ መግደል ሚልዮኖችን ማሥቀየም ነው”አንደኛው አባ ገዳ በኦሮሚያ አባ ገዳዎች ምክር ቤት ላይ የተናገረው። “የኦሮሞን ህዝብ ችግር መንግሥት አያውቀውም ።እኛ ግን እናውቀዋለን ።ህዝቡ በየቀኑ ይነግረናል።”ሌላኛው አባ ገዳ የተናገረው። በነገራችሁ ላይ አሁን … Continue reading

በሳን ሆዜ ከተማ በሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ከፍተኛ የሐገር ፍቅር እና የትብብር መንፈስ በታየበት ሁኔታ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ እሁድ ፌብሩዋሪ 14 ቀን፣ 2016 ከቀኑ 2:00pm 7:30 pm በሳን ሆዜ ከተማ ማሶኒክ ሴንተር፤ የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አራት ተናጋሪ እንግዳወች፣ የእምነት አባቶች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የሰሜን ካሊፎርኒያ ከተሞች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት ሲሆን ከፍተኛ የሐገር ፍቅር ስሜት እና የትብብር መንፈስ በታየበት ሁኔታ ተጠናቋል። አዘጋጅ ኮሚቴውን ወክለው ስብሰባውን የመሩት ዶ/ር አበበ … Continue reading

ያልተሞከረውን ሙከራ : BefeQadu Z. Hailu

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እያለሁ ፖለቲከኛ ከሆነውም ካልሆነውም ጋር በፖቲካ ጉዳዮች እንከራከር ነበር። ከክርክሮች በአንዱ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር እኔ እንደሃይማኖት የማከርረውን “ሠላማዊ ትግል አልተሞከረም” እያልኩ እንደወትሮዬ ስሟገት የደረሰልኝ ብቸኛ ሰው ፍቅረማርያም አስማማው ነበር። ፍቅረ በሙግት ሲያጣድፉኝ የነበሩትን፣ እያንዳንዳቸውን “አንተ ሰልፍ ወጥተህ ታቃለህ? ፓርቲ ተቀላቅለህ ታቃለህ?…” እያለ ቀድመው አፋችን ላይ የሚመጡልንን የሠላማዊ ትግል እንቅስቃሴ የሚባሉትን ሁሉ ሲጠይቃቸው … Continue reading

የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች ከያሉበት ተለቃቅመው እንዲታሰሩ የትግራይ ነፃ አውጭ (ሕወሓት) ሥራ አስፈጻሚዎች ወስነዋል

የልዑል ዓለሜ ዘገባ የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች ከያሉበት ተለቅመዉ እንዲታሰሩ የወያኔ ብሔራዊ መረጃን ተንተርሶ የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ስራ አስፈጻሚዎች በትናንትናዉ እለት ወስነዋል። ” የወልቃይት ህዝብ ሙሉ ለሙሉ በትግሬነቱ አምኖ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል ” በማለት ሪፖርት ለብሔራዊ መረጃ ያቀረበዉ የትግራዩ መስተዳድር ደህንነት ክፍል… የህዝቦችን የእርስ በእርስ መጨራረስ በሚፈልጉ የአርበኞች ግንቦት 7 እና መሰል የአማራ … Continue reading