Uncategorized

በፍርድ ቤት ሰላሳ አንደኛቸው – ኡ ኡ ኡ .. እረ ፍትህ የት ነው ያለሽው? | ግርማ ካሳ

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew

እነ ሃብታሙ አያሌው ፣ ሐምሌ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም ነው የታሰሩት። «መረጃ አሰባስቤ አልጨረስኩም» ፖሊስ ስላለ ብቻ፣ ከአራት ወራት በላይ ክስ ሳይመሰረትባቸው ፣ የዋስታና መብታቸው ተነፍጎ በማእከላዊ እሥር ቤት የስነ-ልቦና የአካል ቶሮቸር ተፈጽሞባቸዋል። ሐምሌ 2፣ ሐምሌ 28፣ ነሐሴ 28፣ መስከረም 22 ፣ ጥቅምት 20 ፣ ጥቅምት 26 በጥቅሉ ለስድስት ጊዜ ፍርድ ቤት ከተመላለሱ በኋላ «ከግንቦት ሰባት ፣ ደሚት … ጋር ትሰራላችሁ ፣ ሽብርተኞች ናችሁ» በሚል የሽብርተኝነት ክስ ይመሰረትባቸዋል። ከማእከላዊ ወደ ቂሊንጦ እሥር ቤት ይዘዋወራራሉ።

ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መጉሏሏቱ አላቆመም። ይኸው ኃዳር 2፣ ታህሳስ 9፣ ታህሳስ 15፣ ታህሳስ 24 ፣ ጥር 7፣ ጥር 26፣ የካቲት 11 ፣ የካቲት 25 ፣ በጥቅሉ ዘጠኝ ቀናት ፍርድ ቤት ከተመላለሱ በኋላ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በቀረበባቸው ክስ እስረኞቹ ጥፋተኛ አይደለንም የሚል ቃል ይሰጣሉ።

ችሎቱ ‹‹ለአንድ ወር የለንም›› ካሉ በኋላ 15 የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለግንቦት 13፣ 14 እና 17 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

የቀጠሮ ቀን ሲደርስ እንደገና ለሐምሌ 8፣ 9 እና 10 ሌላ ቀጠሮ ይሰጣል። እስረኞች መጉላላታቸው ቀጠለ። በቀጠሮ ቀን አቃቢ ሕግ አስጠንቶ ያዘጋጃቸዉንና እርስ በርሱ የሚቃረኑ ነገሮችን የተናገሩ ምስክሮቹን አቀረበ። ፍርድ ቤቱ ለነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም፣ በቀረበው ክስ ላይ ይከላከሉ ወይንም መከላከል ሳያስፈልጋቸው ይለቀቁ በሚለው ላይ ለመወሰን የብይን ቀጠሮ ሰጠ።
ነሐሴ አንድ ደረሰ፤ ቀጠሮ እንደገና ተራዘመ። ነሐሴ 14 2007 ዓ፣ም ቀን ፍርድ በአንድ መዝገብ ከተከሰሱት ዉስጥ አምስቱን (ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋን ዳን ኤል ሺበሺና መምህር ሰለሞን) መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ይለቀቁ ሲል ብየን ሰጠ። ቢያንስ 22 ጊዜ ፍርድ ቤት ከተመላለሱና ከ382 በላይ በወህኒ ከማቀቁ በኋላ ማለት ነው።

ፍርድ ቤቱ ነጻ ናችሁ አላቸው። ግን ማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤት ዉሳኔ ንቆ አልፈታም አለ። ሶስት ቀናት ከቆየ በኋላ አቃቢ ሕግ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ አቀረበ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት መረጃዎችን ሳይመረምር፣ የእስረኞችን የዋስታና መብት ገፎ፣ ነጻ ናችሁ የተባሉት እስረኞች የመጀመሪያ ፍርድ ቤትን ዉሳኔ አገደ። እስረኞች ለመስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም ተቀጠሩ።

መስከረም 21 ሲደርስ፣ ዳኞች ስልጠና ላይ ናቸው ተብሎ ለጥቀምት 3 ቀን ተቀጠረ።ከዚያ በኋላ ህዳር 3፣ ታህሳስ 15፣ ታህሳስ 29፣ ጥር 10፣ ጥር 24፣ የካቲት 1 ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተመላለሱ። ፍርድ ቤቱ የመጨረሽ ብይን ለመስጠት የካቲት 7 2008 ዓ.ም ቀን ቀጠሮ ሰጠ።

በከፍተኛው ፍርድ ቤት የአቃቢ ሕግ ይግባኝ እየታየ በተጓዳኝ ፣ እስረኞች ከፍተኛው ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃን ፍርድ ቤት ዉሳኔ ያገደበት አካሄድ ትክክል አይደለም በሚል፣ ለሰበር ችሎት አቤቱታ በማቅረባቸው፣ ጉዳዩ በሰበር ችሎትም ይታይ ስለነበረ፣ ሰበር ችሎቱ በየካቲት 1 ቀን፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዉሳኔ በሕግ አንጻር ስህተት እንደነበረ በመወሰን ጉዳዩን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሶ አስተላለፈ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ በየካቱት 3 ቀን 2008 ዓ.ም እስረኞች እንዲለቀቁና ጉዳያቸውን በዉጭ እንዲከታተሉ ትእዛዝ ሰጠ።
ሆኖም አሁን ማረሚያ ቤቱ ነሐሰ 14 ቀን 2007 ዓ.ም የአንደኛ ደረጃ ፍርድ በት ዉሳኔን እንደናቀው፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ቤትን ዉሳኔ በመናቅ እስረኞችን እስከ የካቱት 7 ቀን ጠዋት ማለዳ ድረስ አልፈታም።

እስረኞቹ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተከላከሉ፣ አትከላከሉ የሚል ብይን ለመስማት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ወቅት የማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤትን ትእዛዝ ጥሰው እስረኞችን በካቴና አስረዉ ሲያመጡ፣ ዳኛው ምን ሊሉ እንደሆነ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የምንታዘበው ይሆናል፡:

ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን እነ ሃብታሙ ቢያንስ ከ30 በላይ ፍርድ ቤት የተመላለሱ ሲሆን የነገው የየካቲቱ 7 ቀጠሮ ሰላሳ አንደኛው መሆኑ ሲሆን ከታሰሩ ደግሞ 558ኛ ቀናቸው መሆኑ ነው።

እነዚህ ወጣት ፖለቲከኞች አገር ዉስጥ በሕግ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አባላት ናቸው። የሚናገሩትና የሚጽፉት በድብቅ ሳይሆን በገሃድና በአደባባይ ነበር። ሆኖም ሕወሃቶች መስማት የማይፈልጉትን ስለተናገሩ፣ ሕገ መንግስቱ በሚፈቅድላቸው መሰረት መብታቸውን ስለተጠቀሙ፣ ሽብርተኞች ተብለው፣ በአገራቸው መከራ እየተቀበሉ ነው።

ፍትህን ፍለጋ ከሰላሳ ቀናት በላይ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም በፍርድ ቤቱ ያሉ ዳኞች የሕግ ስነ-ምግባር በሚፈቅደው መሰረት ሕግን ከመተርጎም ይልቅ የገዢዎችን መመሪያ የሚያስፈጽሙ ጥቁር ካባ የከበሱ ካድሬዎች ሆነዋል። ሕሊናቸው ከመስማት ይልቅ ለሆዳቸው ያደሩ ሆነዋል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በአሁኑ ጊዜ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም። ዜጎችን ይታሰራሉ፣ በእሥር ቤት በደል ይፈጸምባቸዋል። ፍርድ ቤት ይመላለሳሉ። ፍትህ ግን የለም !!!!

Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Blog Stats

  • 52,293 hits
Advertisements
%d bloggers like this: