Uncategorized

ካልተስማማን እንደ አገር እንጠፋለን – ግርማ ካሳ

(ከዝነኛው አገር ቤት ከምትታተመዋ አዲስ ገጽ እትም ስድስት የተወሰደ) ። አዲስ ገጽ ላይ የወጡ ሌሎች ጽሁፎችን ለማንበብ ከታች ወደ ተቀመጠው ሊንክ ይሂዱ)

በግምት ከሃያ አራት አመታት በፊት ይሆናል ቀኑ። በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም እንዲኖር ብዙ ጊዜ የሚደክሙና የሚጸልዩ፣ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሚባሉ አንድ መንፈሳዊአባት፣ ምእመናንን ሲያስተምሩ የተናገሩት፣ ሁልጊዜ የማስታወሰዉና የማልረሳዉ አባባል ነበር።

«አዲስ አበባ አንድ ወዳጄ አርፎ ለቀብር ሄድኩኝ። የወዳጄ የቀብር ሥነ–ስርዓቱ ካለቀ በኋላ ሌሎች ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ እኔ በዚያዉ ቆየሁ። በመቃብሩ ቦታያሉትን ኃዉልቶች እያየሁ በድንጋዮቹ ላይ የተጻፉትን የሟቾቹን ስምና መንፈሳዊ ጥቅሶች ማንበብ ጀመርኩኝ። ዞር ስል አንዱ መቃብር ላይ የትግሬ ስም አየሁ። ሄድብዬ ደግሞ እንደኔዉ በ ”ሳ” የሚያልቅ የኦሮሞ ስም ያለበት ኃዉልት አጋጠመኝ። የአማራም የሚመስልም አለ። እንግዲህ አስቡት … ትግሬዉም አማራዉንኦሮሞዉም … ሁሉም በሰላም ተኝተዋል» ሲሉ እኝህ መንፈሳዊ አባት የታዘቡትን ተረኩ። ምን ለማለት ፈልገዉ እንደሆነ መጀመሪያ ላይ አልገባኝም ነበር።

አይኖቻቸዉን ወደ ምእመኑ አድርገዉ «ሙታን አርፈዉ በሰላም ጸጥ ብለዉ ተኝተዋል። እኔ ትግሬ ነኝ፣ አንተ አማራ ነህ፣ ደግሞ ጉራጌ ሆነህ እኔ ጋር ምንታደርጋለህ ? እያሉ አይገፋፉም። በሰላም ጸጥ ብለዉ ነዉ ጎን ለጎን የተኙት» ሲሉ ትምህርታቸዉን ቀጠሉ።

ምእመናን በተመስጦ ያዳምጡ ነበር ። እኝህ አባት ለትንሽ ጊዜ ዝም አሉና ከኪሳቸዉ ዉስጥ ማህረባቸዉን አወጡ። በአይናቸዉ ላይ የነበረዉን እንባ ጠረጉ። ትልቅትንፋሽ ተንፍሰዉ «ታዲያ … እኛ በሕይወት ያለን ሕያዋን፣ በእግዚአብሄር እንድንዋደድና እንድንፋቀር፣ አንዱ ለሌላዉ እያዘነና እየተከባበርን እንድንኖር በመልኩናበአምሳሉ ፈጥሮን፣ ሁላችንም የእግዚአብሄር ልጆች ሆነን፣ ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ሆነን፣ እንዴት አብረን ተፋቅረን በሰላም መኖር ያቅተናል ? ስለምን ሰዉንበስብዕናዉና በኢትዮጵያዊነቱ ከማክበርና ከመቀበል ይልቅ በዘር እየተከፋፈልን እንደጠላት እንተያያለን ? » በማለት ለምእመናኑ ጥያቄዎች አቀረቡ። «ይኼመርገም ነዉ። ይኼ በሽታ ነዉ። ይኼ ከሙታን የባሰን እንደሆንን የሚያሳይ ነዉ። እግዚአብሄር ከዚህ እርግማን ያዉጣን ! እግዚአብሄር አገራችን ኢትዮጵያንምመልካም ጣቶቹን ዘርግቶ ይፈወሳት ? » ሲሉ፣ ምእመናን ከተቀመጡበት ብድግ ብለዉ «አሜን» አሉ።

ከሃያ አመታት በፊት ደግሞ ሌላ የሰማሁት አንድ ታሪክ ነበር። ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ከዘር ጋር በተገናኘ መዘዝ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩኢትዮጵያዉያን ማለቃቸዉ መቼም የሚረሳ አይደለም። (አሁንም ያ አይነት ችግር በአገራችን አለ)

ያኔ በበደኖ፣ በአርባጉጉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ኢትዮጵያዉያን፣ ከኛ ዘር አይደላችሁም ተብለዉ፣ በጭካኔ ከመቶ ሜትር በላይ በሚሆን ገደል ዉስጥ አይናቸዉበጨርቅ ተሸፍኖ፣ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሴቶች ሁሉ ሳይቀር ተወርዉረዋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤታቸዉ ዉስጥ እያሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። በጣም የሚያሳዝንናየማይረሳ ግፍ በኢትዮጵያዎኖች እጅ ኢትዮጵያዉያኖች ላይ ተፈጽሟል።

የቂም በቀልና የዘረኝነት ደመና አገሪቷን በሸፈነበት በዚያን ወቅት፣ በኢሊባቡር ክፍለ ሃገርም ተመሳሳይ ሁኔታ እንዲፈጠር በዘራቸዉ ምክንያት ዜጎች ይጠቁ ዘንድየሚገፋፋ ርካሽ ቅስቀሳ ማድረግ ተጀመረ። (“አማራ” የሚባለዉ ከ”ኦሮሞዉ” ጋር እንዲገዳደል)

የሚያስደንቀዉ ነገር ግን በዚያ የሚኖሩ አበዉና ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችን ሰብስበዉ «ለዘማናት አብረን ኖረናል። ተዋልደናል። ተጋብተናል። የነርሱ ልጆች የኛ ልጆችናቸዉ። እነርሱን ማጥፋት እኛን ማጥፋት ነዉ» ብለዉ ፍቅርንና አንድነትን አስተማሩ። ለዚህ ይመስለኛል በአርባ ጉጉና በበደኖ የታየዉ አይነት እልቂት በኢሊባቡርተፈጸመ ሲባል ብዙ ያልተሰማዉ።

ከሁለት ሺህ አመታት በፊት ወደ ሆነ ሌላ አንድ አስደናቂ ታሪክ ልዉሰዳቹህ። አገሩ በመካከለኛዉ ምስራቅ ነበር። ሁለት ህዝቦች ነበሩ። የመጀመሪያዎቹአይሁዳዉያን ይባላሉ። ሁለተኞቹ ደግሞ ሳምራዉያን ይባላሉ። አይሁዳዉያንና ሳምራዉያን አይስማሙም ነበር። ፊት ለፊት ተያይተዉ እንኳን ሊነጋገሩ፣ አንዳቸዉወደ አንዳቸዉ ምድር አይደርሱም ነበር። በተለይም አይሁዶች ሳምራዉያንን እንደሐጢያተኛ ይቆጥሯቸዉ ስለነበር ፣ ከነርሱ ጋር ከተገናኙ እንደሚረክሱ አድርገዉነበር የሚያስቡት።እዚህ ላይ፣ በዚያን ወቅት የነበረዉ ባህልና ልማድ፣ የጥላቻ፣ የመናናቅና የዘረኝነት እንደነበረ እናያለን። በሰዎችና በሰዎች መካከል የሚለያይናየሚከፋፈል ሰዉ ሰራሽ ትልቅ ግንብ እንደነበረ እናያለን።

በዚህ ወቅት ነዉ እንግዲህ አንድ ሰዉ፣ የነበረዉንና የጊዜዉን ሁኔታ ወደ ጎን በማድረግ፣ አይሁዳዊ ሆኖ ሳለ ሳምራዉያን ወደ ሚኖሩበት ሰማሪያ ክፍለ ሃገርያመራዉ። በዚያም አንዲት ሳምራዊት ሴትን፣ ሲካር በምትባል በሰማሪያ ባለች ከተማ

Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Blog Stats

  • 52,481 hits
Advertisements
%d bloggers like this: