Uncategorized

የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን (ህወሃት) በሰሜኑ በኩል የሚደያረገዉ ዉጊያና ሰራዊቱ

ልኡል አለም

12744651_935686376528083_8707127406221165750_n

መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል።

  • ኤርትራ ለዘመናት የደከምንበትን እና ያጎለበትነዉን ሐገራዊ እድገት ለመቀልበስ አሸባሪዎችን አሰልጥና ወደ ሐገራችን እየላከች አርበኞች ግንቦት 7 በተባለ የሻቢያ ሐይል እየተመታን እንገኛለን በመሆኑም ከኤርትራ ድንበር ዉጭ በገዛ መሬታችን ላይ ገዢ ቦታዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ያደረጉት እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎችን መደምሰስ ዋና አጀንዳን ነው።
  • ኤርትራ የተቀመጠዉ መንግስት በኢትዮጵያ ዉስጥ ለተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ አመጽ ዋነኛ ተጠያቂና ምክንያት ነዉ፣ ይህንን ድርጊት ለአመታት ሲፈጽሙብን ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መልኩ ለማግባባት ብንሞክርም አልቻልንም፣ ዛሬ የኦሮምን ህዝብ በመቀሰቀና መንግስትን በመገልበጡ ሂደት ላይ እየሰራ የሚገኘዉን ሻቢያ ከስር መሰረቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሌላ መተካት አላማችን ነዉ።

የሚል መንደርደሪያ በመሆኑ ምክንያት የመከላከያ ሰራዊቱ በሁለት ጎራ ተከፍሎ እንዲጋጭ አይነተኛ መንገድ ተከፍቷል።

በተለይም የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችና የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገናዊ ተቆርቋሪዎች… ከአመራር ጀምሮ እስከ ጓድ መሪ ድረስ የስልጣን እርከን ዉስጥ የሚገኙ… የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ጦርነት መመረጡ አግባብ አይደለም! አርበኞች ግንቦት7ም ሆነ ኦነግ ወገኖቻችን ናቸዉ መንግስት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ልዩነቶችን ለመፍታት ያደረገዉ ጥረት የለም! ለምን ጦርነት እንደ መፍትሄ ይወሰዳል? በሚል እስተሳሰብ እርስ በእርሱ እየተመካከረ ሲሆን ..ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ሰራዊቱ እየተሰወረ ለመሆኑ ታማኝ ምንጮቻችን ገለጸዋ።

በተለይም ከሁመራ ጀምሮ እስከ አማሃጅር ድረስ ለማጥቃት በዝግጅት ላይ የሚገኘዉ በሜካናይዝድ ክ/ጦር የተዋቀረዉ የተዉጣጣ ሰራዊት በየቀኑ ክፍተት እያመጣ መሆኑ ወያኔን ከባድ ችግር ዉስጥ ከቶታል፣ አንዳንድ አመራሮችን ባለማመን ምክንያት ከፍተኛ ጄኔራሎች መሬት ወርደዉ እየሰሩም እንደሆነ ታውቋል፣ የአየር ሐይል ሄሊኮፍተር አብራሪዎች ቦታ በብዛት በትግሬዎች እንዲያዝ ተደርጓል።

በባድሜ በኩል በተመሳሳይ መልኩ በአየር ሐይል የታገዘ ዉጊያ ለማድረግ ዝግጅቱ እየተጧጧፈ ሲሆን ደብረ ዘይት እና ድሬ ዳዋ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ የአየር ሕይል 70% ለትግራይ ነጻ አዉጭ የስልጣን ማራዘም ፍላጎት ሲባል ብቻ.. ወደ መቀሌ ተወስዶ በባድሜ በኩል የሚወረወረዉን የወያኔ እግረኛና ሜካናይዝድ እንዲያግዝ ንድፉ በወያኔ የጦር መሐንዲሶችና ጄኔራሎች የቀረበ ቢሆንም… በዚህ በኩል ለሚደረገዉ ማጥቃት ሻቢያ ከፍተኛ ዝግጅት እንዳላት እና በዚህ ክንፍ ለምናደርገዉ ማጥቃት በአንድ ብሔር ብቻ ማለትም በትግሬ ህዝብ ብቻ እንደምንዋጋ እንድታዉቁ ምክንያቱም ሌሌች የኢዮጵያዊ ብሔሮች ከእንግዲህ ለእኛ እንጂ ለሐገራቸዉ የሚሞቱ አይመስላቸዉም በማለት የፖለቲካ ወታደራዊ መረጃ ክፍሉ በድፍረት መናገሩን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።

Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

facebook

https://www.facebook.com/

Blog Stats

  • 54,675 hits
Advertisements
%d bloggers like this: