Uncategorized

ከሕይወት ሞትን ለምን? ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2008

ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ አእምሮ ያለው ያስባል፤ ልብ ያለው ስሜቱ ይነካል፤ ዓይን ካላየ፣ ጆሮ ካልሰማ፣ አእምሮ ካላሰበ፣ ልብ ካልተሰማው ሰውን ሰው የሚያደርገው ምንድን ነው? የትናንቱ ችግር መልኩን ለውጦ ሲመጣ፣ ትናንት ተሞክሮ ያልተሳካው የሕገ አራዊት መፍትሔ ዛሬ ዘመን ከተለወጠ በኋላ ይሠራል ብሎ መወራጨት ጥፋት ነው፤ ዓይን እያለ አለማየት ነው፤ ጆሮ እያለ አለመስማት ነው፤ አእምሮ እያለ አለማሰብ ነው፤ ልብ እያለ ስሜት ሲጠፋ ሰዎች ነን ወይ? ብሎ መጠየቅ ግድ ቢሆንም ያሳፍራል፤ካላፈርን ይበልጥ ያሳፍራል፡፡
ከአርባ ዓመት በፊት ለመላው አፍሪካ የሽማግሌና የአስታራቂ አገር የነበረችው ኢትዮጵያ በተከታታይ የአረም ጎረምሶች ትውልድ ተወርሳ እንኳን ለአፍሪካ በአጠቃላይና ለራስዋም የምትበቃ አልሆነችም፤ በአረም የተወረረች አገር!
ይኸ ሁሉ ትርምስ፣ ይኸ ሁሉ ጭካኔ፣ የማንን ጥቅም ለማስከበር ነው? ማንን ገድሎ ማንን ለማዳን ነው? ማንን አደህይቶ ማንን ለማበልጸግ ነው?
ትርፉ በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ የሚከተል ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ችኮ ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ነው፤ የተገኘውም ሀበት ቢለብሱት እከክ፣ ቢበሉት ቃር እየሆነ በጸጸት አለንጋ እየተገረፉ መኖር ነው

Discussion

3 thoughts on “ከሕይወት ሞትን ለምን? ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

  1. So called profesr Mesfen only care about power .because about two years ago he hated Banda Essayass now profesr love Banda Essaya s even he lionizing Banda Essayass .
    I don’t except from naftnga Masfen an ounce of principle.
    Because he has a mantality of Banda minlk you even sell your Owen country to Italian and French .Rember there were so called Ertirea during the really Ethiopian king Yohans who died fighting for his country .Banda minlk is the frist Ethiopia to sell country to white man Italian and French .
    Whe the really hero like Alula and Tigray people fighting against Italian .
    Banda Minlke sold Djibouti to French

    Like

    Posted by Solomon | February 28, 2016, 8:41 am
  2. ፕሮፌሰር፥ ችግሩ ያለመታደል ነው ። በገዳዮቹም በተሰላፊዎቹም መፍረድ ይከብዳል ፥ ችግሩ ያለው በአስላፊዎቹና በአስገዳዮቹ ላይ ነው ። ለአለቆቹ የህይወት መጥፋት ከቁጥር አይዘልም፡ አላማው ስልጣን ነው ። እንደ ሀገር ሁነን ስናስበው የሁለቱም አሁን ያለው አካሄድ “ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመርጡ ነው” አሁን ዘወር ብለን ስናስበው እነዚህ ስብስቦች ከደርግ አምባ ገነን ስርአት በምን ይሻላሉ። የእውነት የሀይማኖት መሪዎች ካሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለርቅና ለሰላም ቢሰብኩ እየመጣ ካለው እልቂት ለመትረፍ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የዘር ፖለቲካ ለሀገሪቱ አይበጅም ከመተላለቃችን በፊት በቃህ እንበለው!!!!

    Like

    Posted by Molla | February 28, 2016, 12:17 pm
    • Mr Mola ,you don’t know Ethiopian history.
      You only know Banda Minlk Ethiopian history .written by minlk historian ..
      I call Minlke Banda because Minlke is the only Ethiopian king to sell Ethiopian land to white Italian and French .
      Banda Minlke sold Tigray Ethiopia land now Ertirea to Italian .
      He sold Djibouti Ethiopian port to French .
      To people like you minlk still is a hero ,afte the crime minlk committed on Ethiopia..
      A lot of people minlk is a hero because minlk speak the Neftgna talk.
      Minlk sold Tigray Ethiopia land and port to Italian because his agenda were to divided and concur Tigrayn because were challenging him because tigryan were the relly kingdoms root .the kingdom comes from king of king Yohans .

      Like

      Posted by Solomon | March 1, 2016, 11:29 am

Leave a reply to Solomon Cancel reply

facebook

https://www.facebook.com/

Blog Stats

  • 75,612 hits