Archive for

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እገዳ በፓትርያርኩ ትእዛዝ ተነሳ

ዛሬ በኢትዮጵያ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ለልጃቸው ሕክምና ችየገንዘብ ርዳታ የወሰኑላቸውን የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም 10 የአስተዳደር ኮሚቴ አባላትን  ከሥራና ከደሞዝ ያገዱ ቢሆንም ፓትርያርኩ እግዱን ሽረውታል፡፡ ሥራ አስኪያጁ፣ “ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ” በሚል ገንዘብ በማሠባሰብ ላይ እንደነበሩ መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት … Continue reading

ስለ ተመስገን ለምን እንደምፅፍ | ከታሪኩ ደሳለኝ

ተመስገን እስካሁን የታሰረባቸውን 1 ዓመት ከ5 ወር ከ14 ቀንናት በንግልት ውስጥ አሳላፏል። እያሳለፈም ነው። በነዚህ ግዚያት ውስጥ መንግስት ሲያሻው ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ እንዳይጠይቀው ሲል ሲፈልግ ከቤተሰብ ውጪ ማንም እንዳያየው ሲል ሲያሰኝው ደግሞ ተመስገን አአስሮ ብቻ ማስቀመጤ ስላላረካኝ በማለት እንዴ ጭለማ ቤት አንድ ግዜ ቅጣት ቤት አንድ ግዜ አደገኛ የእስር ክፍል የሚለው ውስጥ ሲያንገላታው ከርሟል። እየከረመም … Continue reading

ሕወሓቶች ገዱ አንዳርጋቸውን አንገቱን ለማስደፋት ዘምተዋል | “ግንቦት 7 ነው… የአንዳርጋቸውን ራዕይ እያስፈጸመ ነው” እያሉ እየወነጀሉት ነው

ወልቃይትን ጨምሮ በአማራ ክልል እየተነሱ ያሉትን የመብት ጥያቄዎች ተከትሎ ሕወሓቶች “ገዱ አማራውን በትግራይ ሕዝብ ላይ እያስነሳው ነው” የሚሉ ዘመቻዎችን መክፈታቸው ታወቀ:: ይህም ዘመቻዎች የአማራ ክልል ር ዕሰ መስተዳደርን አንገት ለማስደፋት የታቀደ ሲሆን ዘመቻው በድርጅቱ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሶሻል ሚድያዎችም ጭምር ተጀምሯል:: ከሕወሓቱ አባይ ወልዱ ጽህፈት ቤት በወጣ ትዕዛዝ የወልቃይትን እና ሌሎች የአማራ ሕዝብን ጥያቄ ተከትሎ … Continue reading

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በ500 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት፣ የአክሰስ ሪል ስቴት መሥራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በ500 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ሐሙስ መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ወሰነ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል መርማሪ ቡድን ግን የአቶ ኤርሚያስን በዋስ መፈታት በመቃወም አቤቱታ ቢያቀርብም፣ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡ የምርመራ ቡድኑ አቶ ኤርሚያስ ቤት ከሚያሠሩ ደንበኞች ላይ በቢሊዮን … Continue reading

የሽብርተኛ ትርጉም – መስፍን ወልደ ማርያም

መጋቢት 2008 የሚማር የለም እንጂ የሚማር ቢኖር የሽብርተኛነትን ትርጉም ሰሞኑን በቤልጂክ እያየንና እየሰማን ነው፤ በኢትዮጵያ ያሉ የእውቀት ምልክቶችን በዶላር እየገዙ ስማቸው ላይ የለጠፉ ጉልበተኞች ተናገርክ(ሽ) ብለው ብቻ ሳይሆን አሰብህ(ሽ) ብለው ሰፋፊ እስር ቤቶች እያሰሩ ወጣቶችን ሲያጉሩበት ምክንያታቸው ሽብርተኛነት ነው፤ ሽብር ማለት ሰሞኑን በቤልጂክ አውሮጵላን ጣቢያና በባቡር ጣቢያ ላይ እንደታየው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም፤ ከታየም በአገዛዙ … Continue reading

ሰበር ዜና: ዶክተር መረራ ጉዲና ከሀገር እንዳይወጡ ተደረገ።

<<ዶክተር መረራ ጉዲና ከሀገር እንዳይወጡ ተደረገ። ወደ አሜሪካ ለመምጣት ትላንት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሄዱም መውጣት አልቻሉም። ዛሬ ወደ ኢሚግሬሽን ሄደው ሃላፊው ስብሰባ ገብተዋል ተብለው ተመልሰዋል። ”ፓስፖርትዎን መሳሪያው ማንበብ አልቻለም። ምናልባት ሽቶ ነክቶት፡ ወይም ዘይት ተደፍቶበት ሊሆን ይችላል።” ቦሌ የኢሚግሬሽን(ደህንነት) አንድ ሰራተኛ የተናገረው>>ESAT .

የት ነው ያለሁት? እንዲሁ ይጨንቀኛል! – ነፃነት ዘለቀ

ሰሞኑን ልክ አይደለሁም፡፡ መላ ሰውነቴ ልከ አይደለም፡፡ እጅግ ይጨንቀኛል፡፡ ያ ደደብ ደም ብዛት የሚሉት በሽታ ሊይዘየኝ ይሆን እያልኩም እጨነቃለሁ፡፡ የጭንቀት ጥበቴን መነሻ ግን አውቀዋለሁ፡፡ መፍትሔ የሌለው መሆኑ ስለሚሰማኝ ግና እየባሰብኝ እንጂ እየቀለለኝ ሲሄድ አይታይም፡፡ በተረቱ “የጨው ተራራ ሲናድ ብልህ ያለቅስ፣ ሞኝ ይስቅ” ይባላል፡፡ በኢትዮጵያ የቁም ሞት የምንበሳጭና ተበሳጭተን የበኩላችንን አስተዋፅዖ የምናደርግ በጣም ጥቂቶች ነን – … Continue reading

የመቐለ ባለ ባጃጆች ኣድማ መትተዋል። ሁለት የዓረና ከፍተኛ ኣመራሮች ታሰሩ

ከዛሬ 14 / 07 / 2008 ዓ/ም ረፋድ የጀመረው የባለ ባጃጆች ኣድማ “እንደ ሚኒባስ ታክሲዎች ታፔላ ኣበጅታቹና በስምሪት ብቻ መስራት ኣለባቹ” የሚል ኣዲስ ኣሰራር በመቃወም የተመታ ኣድማ ነው። ዛሬ እሮብ መቐለ ከተማ ባጃጆች ምንም ዓይነት እንቅሴቃሴ ኣይታይባቸውም። ከሁለት ሺ ኣምስት መቶ በላይ የሆኑት ባለ ባጃጆች “እምቢ ለመብቴ” ብለው በውሳኔያቸው ፀንተዋል። መቐለ ከተማ ከፍተኛ የህዝብ ትራንስፖርት … Continue reading

ፍትሕ ሚኒስቴርን የሚያፈርስ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

በምትኩ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሊቋቋም ነው ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሥነ ምግባር ላይ ብቻ እንዲያተኩር ይገደዳል ፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊሆን ነው የፍትሕ ሚኒስቴርን የሚያፈርስ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በምትኩ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋምን ለመመሥረት የሚያስችል ሌላ ረቂቅ አዋጅም ለፓርላማ ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀርቧል፡፡ ፓርላማው ከቀረቡለት በርካታ ረቂቅ አዋጆች መካከል … Continue reading

ቤተ አምሃራ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትን ትግል በማስመለከት ብአዴንን አስጠነቀቀ – “የአማራ ህዝብ ቁጣ ለመትረፍ ከህዝባችሁ ጎን ቁሙ”

  ቀን: መጋቢት 13 2008 ዓ. ም ወቅታዊውን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ የማንነት ትግልን በማስመልከት ከቤተ አማራ የተሰጠ መግለጫ ፦ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ የትግሬ – ወያኔ ሽፍታ ስርዓት በጉልበት የጫነባቸውን ባዕድ ማንነት በመቃወም የተፈጥሮ ማንነታቸው የሆነውን አማራነት ጥያቄ ያቀረቡት እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደነበር ይታወቃል:: ይህም የታላቁ አማራ ህዝብ ለዘመናት የኖረበትን ከፍተኛ የሞራል ደረጃ … Continue reading

ለተቃውሞ የተዘጉት ከሁመራ ወደ ጎንደር ፣ ከሰረቋ አርማጭሆ የሚወስዱት መንገዶች በሃገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት ተከፈቱ

የሚሊዮኖች ድምጽ እንደዘገበው ከሁመራ በቅርብ እርቀት የምትገኘው በአከር ከተማ በደረሰን መረጃ ሕዝቡ በጉልበት አታስገድዱን እኛ ጎንደሬወች ነን በማለት ከሕወሃት ጋር ከትላንት ማምሻዉን ጀምሮ እንደተፋጠጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። በአዲ ጎሹ በኩል ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚያስገባው አውራ ጎዳና እና እንዲሁም በተጨማሪ በዳንሻ በኩል ከሁመራ ወደ ጎንደር ፣ ከሰረቋ አርማጭሆ የሚወስዱት መንገዶች በሕዝቡ እስከ ትላንት ማምሻዉን ድረስ ተዘግተው ነበር። … Continue reading

ሰበር ዜና : በዳንሻ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ባዶ እጃቸውን ባሉ የወልቃይት አማሮች ላይ እየተኮሰ ይገኛል::

በዳንሻና በሶሮቃ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ አለ፡፡ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ከሦስት ቀናት በፊት አቶ ሊለይ ብርሃነ የተባለን የወልቃት አማራ አፍኖ ወስዶ የት እንዳደረሰው ባለመታወቁ ምክንያት በሕዝቡ በተቀሰቀሰ ቁጣ በዚህ ሰዓት በአካባቢው ችግር እንደተፈጠረ በስልክ እየተነገረኝ ነው፡፡ሲል የቀለም ቀንድ ጋዜጣ አዘጋጅ ሙሉቀን ተስፋው ጽፏል:: ወዳጆች ሆይ የታጠቀ የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ ባዶ እጃቸውን ባሉ የዳንሻ … Continue reading

መታሰር ምንም ማለት አይደለም። አስሮ ሰብአዊ መብትን መጣስ ግን የትም ሀገር የለም! ከአጥናፍ ብርሃኔ

እንደኢትዮጵያ መንግስት ጨካኝ የለም። 4 በ5ሜትር በሆነች ቤት ውስጥ የምንኖረው 23 ሆነን ነው። እዛችው ቤት ውስጥ ለሽንት የምንጠቀመው ባልዲ ነው፣ የሁላችንም ልብስ አንድ ላይ ይቀመጣል። ይህን ተቃውመን የርሀብ አድማ ብናደርግ ‘ከፈለጋችሁ መሞት ትችላላችሁ’ ነው የተባልነው። እኛም ለመሞት ዝግጁ ነን።” ይህን የተናገረው በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ነው። ……… በኢትዮጵያ ላለው መንግስት ሰብአዊ መብት ቅብጠት … Continue reading

ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው ለመመሰስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገችውን ስምምነት የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ በታላላቅ የኖርዌይ ከተሞች ተካሄደ!!

ኢትዮጵያውያን በስደት ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሀገሮች አንዷ የሆነችው ኖርዌይ ስትሆን በኖርዌይ ሃገር ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ስደተኞች ይገኛሉ። እነዚህ ስደተኞች ከሌላው ሀገር ለየት የሚያደርግ ጠንካራ የፓለቲካ አቋም ያላቸው መሆኑም ይታወቃል። ስደተኞቹ በተለያየ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጡ የፓለቲካ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል። ሆኖም ግን የኖርዌ መንግስት እ.ኤ.አ በ2012 ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር … Continue reading

በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ | ምስጢራዊ መረጃ

ከዚህ በታች የምታነቡት በትግረኛ ተጽፎ የህወሓት ባለስልጣናት የተወያዩበትና የተስማሙበት ድብቅ መረጃ ነው። ይህ ረቂቅ ዶኩመንት በወያኔም ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ በተግባር በአስቸኳይ በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ በተግባር ላይ እንዲውል ስምምነት ተደርሶበታል። ይህ በትግረኛ የተዘጋጀውና ወደ አማርኛ የተተረጎመው ሰንድ የተዘጋጀውና በህወሃት ባለስልጣናት እንዲተገበር ያቀረበው በብዕር ስሙ ዘጽኣት አናንያ በሚል ስም የሚታወቅ እውነትኛ ስሙ ግን … Continue reading

ወልቃይት ፀገዴና ፀለምት፥ በዐይኔ ካየሁትና ከታዘብኩት በያሬድ ጥበቡ

መጋቢት 1 ቀን 2008 አም መግቢያ የዛሬ 39 አመት ግድም ለሶስት አመታት ያህል ከሰኔ 1969 እስከ ሰኔ 1972 አም ድረስ በፀለምት፥ ዋልድባ፥ ቆላወገራና ወልቃይት ውስጥ የኢህአፓ ሰራዊት አባል በመሆን በእግሬ ተጉዣለሁ ። በአማካይ በቀን 5 ሰአት እንጉዋዝ ስለነበር ፥ በአመት 9000 ኪሎሜትር፥ በሶስቱ አመት ቆይታዬ 27000 ኪሎሜትር ያህል መንገድ ተጉዣለሁ ማለት ነው። ዛሬ እነዚህ አካባቢዎች … Continue reading