Uncategorized

በኦሮሚያ ክልል ሹምሽር ተካሄደ | ተጨማሪ ባለስልጣናት ከቦታቸው ተነሱ

ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው የኦህዴድ የከተሞች ዘርፍ የፖለቲካ የድርጅት ኃላፊ አቶ ለሲሳ ሃዩ ተነስተው በምትካቸው የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በነበሩት ሳዳ ነሻ ተተክተዋል።

OPDO 5

እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የነበሩት አቶ በዙ ዋቅቢሳ የኦሮሚያ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ በዚህ ቦታ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሰለሞን ከቹማ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ በመሆን ተመድበዋል።

በኦሮሚያ ክልል ኦህዴድ ያካሄደው ሹምሽር ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ምንጫችን ጨምሮ ገልጿል።

የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የተመደቡት አቶ በከር ሻሌ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ትላንት ከሰዓት በኋላ ድረስ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት ሥራቸው ላይ የነበሩ ሲሆን በእርሳቸውም ቦታ እስካሁን የተተካ አዲስ ሰው አለመኖሩ ታውቋል።

አቶ በከር በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን አቶ መላኩ ፈንታን ተክተው ወደ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተሹመው ከመምጣታቸው በፊት የአዳማ ከተማ ከንቲባ ነበሩ። ከዚያም ቀደም ብሎ የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማኀበር ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆንም አገልግለዋል።

Discussion

No comments yet.

Give a comment

facebook

https://www.facebook.com/

Blog Stats

  • 75,612 hits