Uncategorized

ዘላለማዊ ክብር በታላቅ መስዋእትነት ድንበራችንንና ነጻነጻችንን ላስጠበቁ የአድዋ ጀግኖች!! ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

እንኳን ለአድዋ ድል አንድ መቶ ሀያኛ አመት አደረሰን፡፡ እንዲህ ያለው ቀን ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ባንዲራችን የሚውለበለብበት ኮረብታ፣ ከብቶች የተሰማሩበት መስክና አራዊት የሚተራመሱበት ዱር ገደል፣ ውለን የምናድርበት ቀዬ ከአለትና ከአፈር ብቻ ሳይሆን፣ ከአባቶቻችን ደምና አጥንት የተሰራ መሆኑን እንድናስድ ያደርገናልና፣ ‹‹እንኳን አደረሰን!››፡፡
.
ይህ ቀን አባቶቻችን የሀገራቸውን ዳር ድንበር ላለማስነካት፣ ነጻነታቸውን ላለማስገሰስ፣ ተማምለው ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀን ጠላት በጦርና በጎራዴ ገጥመው፣ እንደ አሸን ረግፈው ድል ያደረጉበት ቀን ነው፡፡ የዚህን በረከታቸውን ዋጋ የምናውቅ ደግሞ፣ በዚህች ቀን እነሱ ያወረሱንን ሀገርና ነጻነት ጠብቀን፣ ለልጆቻችን ለማውረስ ቃልኪዳን (ቢያንስ ለራሳችን- በነገራችን ላይ እውነተኛው ቃልኪዳን ለራስ የሚገቡት ነው) መግባት ይጠበቅብናል፡፡
እንዲት ሀገር ክብርዋንና ነጻነቷን ጠብቃ፣ በልማትና በስልጣኔ ተራምዳና ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደርን የህዝቦችዋ የመተዳደሪያ ካስማ አድርጋ እንድትኖር ጀግኖች ያስፈልጓታል፡፡ ዳር ድንበራቸውንና ነጻነታቸው ለመጠበቅ እንደ አባቶቻችን ህይወታቸውን ለመክፈል የማይሳሱ ጀግኖች፣ እንደወንድሞቻችን ለዲሞክራሲና ሀሳብን ለመግለጽ ነጻነት በመታገል በየእስር ቤቱ ስቃይን ለመጋፈጥ ብሎም ህይወታቸውን ለመክፈል ወደኋላ የማይሉ ጀግኖች፣ በገጠርና በከተማ፣ የበረሀውና ሸንተረሩ ወገናቸውን ከችግር ለማውጣት ደፋ ቀና የሚሉ የልማት ጀግኖች ያስፈልጓታል፤ . . . . ሀገር እነዚህ ሁሉ ጀግኖች ያስፈልጓታል፡፡ አንዱ ጀግና ሌላውን አይተካም፡፡ ዲሞክራሲና ቢሰፍን፣ አገር ቢለማ ድንበር ካልተከበረ ዋጋ የለውም፡፡ ድንበርን ምን ቢያስከብሩት፣ ዲሞክራሲያዊና መልካም አስተዳደርን የተመለኮዘ ልማት ከሌለ፣ አገር በግንብ የታጠረ በረት ህዝቡም በበረቱ ውስጥ እንደተከረቸመ ከብት ነው፡፡ .. . . ለዚህ ነው ሀገር የጦር፣ የዲሞክራሲና የልማት ጀግኖች የሚያስፈልጓት፡፡
.
ነፍጠኛም በሉኝ የድሮው ስርአት ናፋቂ . . . ወይም ሌላ፣ የአድዋ ጀግኖቻችንን ማክበር የምፈልገው ከመሪዎቻቸው የክተት ጥሪ፣ ከፈረሰኛው ማስገምገም፣ ከጀሌው (ባላገሩ) ሽለላ፣ ቀረርቶና ፉከራ ጋር ነው፡፡ የወረወሩት ጦር አየሩን ሲሰብቀው፣ የፈረሱ ኮቴ አዋራውን ሲያጤሰው፣ የጀሌው ባዶ እግር ጋሬጣውን ሲገነጥለው . . . . . አንድ ጦር በጠላት ደረት ለመሰካት ሁለት ሶስት ሆኖ ሲወድቅ፣ . . . የአድዋውን ጀግና ማክበር፣ ማሰብ ያለብን እንዲያ ነው! ያንን ስናስብ . . .ያንን ስናከብር የመስዋእትነቱ ክብደት ይታሰበናል፤ ጀግንነቱም ይታየናል፡፡ ይህ ግን አልሆነም! ፉከራውና ቀረርቶው የለም፤ ቢኖርም ልማታዊ ‹‹ጀግኖቻችን›› የሚወደሱበት ነው፡፡ ታላላቅ ባለስልጣኖቻችንና ‹‹አንዳንድ የየከተማው ነዋሪዎች›› የአድዋ ድል ለልማታችንና ለእድገታችን መሰረት መሆኑን በየዜናው ማሰራጫ ሲናገሩ ሰማሁ፡፡ በዚሁ ከቀጠልን የሚቀጥለው ትውልድ የአድዋ ድል አባቶቻችን ግድብ ሲሰሩ በደራሽ ውሀ የተወሰዱበት ሊመስለው የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም፡፡
.
በእርግጥ ኢህአዴግ ራስወዳድ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያ የቆመችው እነሱ ደርግ ላይ በተቀዳጁት ድል ብቻ ይመስላቸዋል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ መንገድና ድልድይ መሰራት የተጀመረው ከሀያ አምስት አመት ወዲህ ይመስላቸዋል፤ የሀገር እድገትም ሆነ ውድቀት ከዘመን ዘመን የሚሸጋገር፣ ቀጣይ ሂደት መሆኑን እንደምን እንደማይገባቸው አይገባኝም፡፡ በእርግጥ ከሀገሪቱ እድሜ አንጻር ሲታይ፣ ነጥብ በምታክል ጊዜ ውስጥ፣ ሀገሪቱን የባህር በር አልባ ያደረገ፣ ድንበሩን ለመደራደሪያነት አቅርቧል እየተባለ የሚታማ መንግስት በአድዋን ጀግኖች መስዋእትነት ባይፎክርና ባይሸልል፣ ግድብ ቢያቆምበት ወይም ሀዲድ ቢዘረጋበት አይገርምም፡፡
.
ዘላለማዊ ክብር በታላቅ መስዋእትነት ድንበራችንንና ነጻነጻችንን ላስጠበቁ የአድዋ ጀግኖች!!

Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

facebook

https://www.facebook.com/

Blog Stats

  • 54,681 hits
Advertisements
%d bloggers like this: