Uncategorized

ምስጋና ለአድዋ ልጆች:: ታምራት ነገራ

የአድዋ ድል ለእኔ ለእኛ ትርጉሙ ምንድን ነው ? ይሄን ጥያቄ መጠየቅም ሆነ በእዚህ ጥያቄ ዙሪያ መከራከር ለየትኛውም ኢትዮጵያዊ አካዴምያዊ ልምምድ ብቻ ሳይሆን የህልውና፤ የማንነት እና የዜግነት ግዴታም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ይገባልም፡፡ ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳው እጅግ ታላቅ ስለሆነው አድዋ ቀርቶ ስለማንኛውም ነገር ስንወያይም ሆነ ስንከራከር የምንወያበት እና የምንከራከርበት አውድ ከርእሰ ጉዳዩ ያላነሰ ትኩረት ይገባዋል፡፡
የደርግ አመራር ፖለተካዊ፤ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስህተቶች እንዲሁም የእኛ ትውልድ የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥፋቶች ተደማምረው በአሁን ወቅት ኢትዮጵያን እየመራ ያለው ኃይል እንኳንስ ለአድዋ ተገቢውን ክብር ሊሰጥ በአድዋም በኢትዮጵያዊነቱም ማፈር ዳር ዳር የሚለው የተቀመጠበትን ሕብረብሔራዊ መንበር በመገዝገዝ የተካነ የታሪክ ጉድ ነው፡፡
ይህ የፖለቲካ ኃይል በአድዋም ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ የማፈሩን ጨዋታ ቢካንበትም ስልጣኑን ተጠቅሞ በትምህርት ፖሊሲ፤ በመገናኛ ብዙሃንን የአገር አስተዳደር ፖሊሲውን በኩል በአድዋ ድል የሚያፍር፤ ይህን አፍረቱንም እንደ ክብር የሚቖጥር ትውልድ መፈልፈል ግን ችሏል፡፡ ይህ ፖሊሲ የበደለው ትውልድ እንደ አስፈላጊነቱ እንደስፍራው ሊታዘንበትም ሊታዘንለትም ይገባል፡፡
የዚህ ፖሊሲ የበደለው ትውልድ ነጂዎች በአድዋ ዙሪያ አመት እየጠበቁ የሚፈጥሩት አተካሮ ግን በኢትዮጵያ ያለው የትውልድ በአድዋ የሚያፍረው ብቻ ሳሆን በአድዋ የማይደራደር፤ አድዋን ለማስታወስም ሆነ ለማወደስ መንግስትንም ሆነ ፓርቲን የማይጠብቅ ትውልድ ኢትዮጵያ እንዳፈራች እያየን ነው፡፡
እነዚህ እውነተኛ የአድዋ ልጆች የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት በመንግስት ፖሊሲ በተጠቃበት፤ በቆሰለበት ዘመን መገኘታቸው እና አንገታቸውን ቀና ማድረጋቸው ኢትዮያዊ ብሔርተኝነት ተስፋው ፤ ዘመኑ፤ እሳቱ ገና እየለመለመ እንደሚሄድ ትልቅ ምስክር ናቸው፡፡ ከሰሞኑ አድዋ ተቀናቃኞች ትንኮሳ የወሰድኩት ትልቁ መልዕክት አድዋ አሁንም እየወለደች እንደሆነ አድዋ እንዳልመከነች ነው፡፡ በአገር መንግስት መጨቆንን ከ ባእድ ቅኝ ግዛት የማያምታታ ምርት ትውልድ አሁንም አለን፡፡
በአድዋ ጦርነት ጊዜ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ስለተከተለው ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ እስትቴጂ ፤ አድዋ በዘመናዊት ኢትዮጵያ አፈጣጠር ላይ ያበረከተው በረከትም ሆነ እዳ ካለ በእዚህ ዙሪያ መነጋገገር መከራከር ምንም ክፋት የለውም፡፡ እኔም እራሴ በዚህ ዙሪያ ተከራክሬ አውቃለሁ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ዛሬም ስለአድዋ ለመናገር ለመከራከር ደስተኛ ነኝ፡፡
አድዋ ላይ ስከራከር ግን ለማንኛውም ርዕስ ጉንጬን ለማልፋት እና ጊዜዬን ለማጥፋት ፈቃደኛ አይደለሁም ፡፡ ለምን አያቶቼ ከሚኒሊክ ጋር ዘመቱ፤ በጣልያን ቕኝ መገዛት ይሻላቸው ነበር የሚል የነቃህ የሚያስመስል አተላ ይዘህ እንድትከራከረኝ አይደለም እፊቴ እንድትቆም አልፈቅድልህም፡፡ የመናገር መብትህ እንዲጠበቅ ስለሚያሳስበኝ ይህን አተላህንም ብትናገር እና የአንተ ቢጤ አተላ አድናቂዎች ጋር ብትጎነጨው መብትህ ነው፡፡
ኢትዮጰያም ላይ ሆነ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ላይ እንድታናፋ ቀን ፈቅዶልሀል እና ዘመንህን አጣጥም፡፡ እኔም ቁስሌን እያከምኩ ቀኔን እጠብቃለሁ፡፡
ከዘመኑም ከንግሰትም ታግላችሁ አድዋን ለማስታወስ የተቻላችሁን ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ታላቅ ነው፡፡
ለኢትዮጵያ ለተዋደቁ አባቶቻችን ዘላለማዊ
Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

facebook

https://www.facebook.com/

Blog Stats

  • 54,681 hits
Advertisements
%d bloggers like this: