Uncategorized

የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው (ሄኖክ የሺጥላ )

minilik

ኣጤ ምኒልክን ሲወቅስ 100 ኣመት የፈጀው ትውልድ ፥ እሱ የኖረበትን መቶ ኣመት ምን ሰራበት ? ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴን ሲተች የኖረው « ያ ትውልድ » ንጉሱ ከወደቁ ወዲያ እሱ የኖረበትን 42 ኣመታት ምን ጠቃሚ ነገር ኣደረገበት ? ደርግን 17 ኣመት በርሃ ሲታገል የኖረው ህውሃት ስልጣን በእጁ ላይ ኣስገብቶ የኖረበትን 25 ኣመታት የእርዳታ ስንዴ ከመለመን ውጪ ፥ የቀደሙ ስርዓቶችን በደልን እየዘከዘከ ፥ ባለፈ ስርኣት በደል ኣይን ንፁህ ነኝ ቢለንም በስራው ስንለካው ፥ ጨካኝ ከሚባለው የደርግ ዘመነ መንግስት የባሰ ጠርናፊ እና ገዳይ መሆኑን ነው ያየነው ።

እኛስ 25 ኣመት በኣንድ ጨቋኝ ስርኣት ክርን ስንደቆስ ፥ እንደ ባቢሎኖች መግባባት ኣቅቶን ከመናከስ ውጪለሃገራችን የሚበጀውን ነገር ለማድረግ ምን ሰራን ? የሃገራችን ቁስል የውሻ ቁስል እንዲሆን ኣንድነትን ከመምረጥ ይልቅ ፥ በክክል በጎጥ በብሄር ተቧድኖነን ፥ በቁስላችን ላይ እንጨት እየሰደድን ፥ ማንነታችንን መርዘኛ የጎሳ ተውሳክ እንደ ማር ኣልሰን ፥ በቀበሌ ልክ ሃገር መስለን መታየት ኣሻን እንጂ ፥ እንደው ምን ሰራን ?

ትናንት ቤተ እምነቱን በመናቅ ፥ የሶሻሊስት እምነት ኣራማጆች የነበሩት ፥ በሃሉን ለማያከብሩለት ህብረተሰብ ስለ ህብረተሰባዊነት እየደሰኮሩ፥ እምነቱን የግሪክ ኣማልክት ዘመነኛ ተረት እንደሆነ በኣደባባይ እያወሩ፥ ስለ ኣንድነት ቢሰብኩም ፥ ስለ ሃገር ፍቅር እጃቸውን « ኢትዮጵያ ወይም ሞት » ብለው ወደ ሰማይ እንደ ሮኬት ቢለቁም ፥ ኢትዮጵያ ሳትሞት እነሱ ግን ካፈሯ ስር ተቀብረዋል ። ዛሬም የለውጥ ፥ የእድገት ፥ የመሻል እና የመሻሻል ማሳያዎቻችን በሰው ላይ ሳይሆን በድርብርብ ብሎኬቶች የተሰሩ ፎቆች ማንነት ላይ የቆሙ በማስመሰል ፥ ህዝቡ እየተራበ « ልማት » ብለው ሲደሰኩሩ ፥ ንፁሃን ዜጎቿን እንደ ከብት በ ቃጫ እያሰሩ የብሄር ብሄሬሰቦች መብት እያሉ በሃገር ዱካ ላይ ሲያሴሩ እያየን ነው ። እጅግ የሚያሳዝነው ደሞ ቢያንስ ሰው መሆናቸውን ኣለማወቃቸው ፥ ደካሞች ፥ ተሰባሪዎች ፥ ሟቾች መሆናቸውን ኣለመገንዘባቸው ።

እኛ ዛሬ ላይ ኣድራጊ ፈጣሪዎቹ ፥ ዛሬ ላይ ባለ ጉልበቶቹ ፥ ዛሬ ላይ ባለ ሰራዊቶቹ ፥ ያለፈውን ስንጠላ ፥ ስናጣጥል እና ስናብጠለጥል እኛ ግን በነበርንበት ዘመናችን ፥ በኖርንበት የጉብዝና ወራታችን ምን ሰራን ? የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው።

ለሁሉም ነገሮች መልስ ኣለኝ ለሚል ግን ኣንዱንም መልሶ ለማያውቅ ስርኣት እኛ የምን ኣይነት ቅሌታም መንፈስ ባለቤቶች ብንሆን ነው ይህን ሁሉ ዘመን ድንቁርናውን ተስፋ ኣድርገን የኖርነው ? በየትኛው የጀግንነት ስሌት ነው ሚኒሊክን የሚረግሙ ኣንደበቶች ለወያኔ ተንበርክከው የሚገዙት ? በየትኛው የሰውኛ ሂሳብ ነው መንግስቱ ሃይለማሪያምን ኣሰይጥነው የሚያቀርቡ ሚዲያዎች ስለ መለስ ራዕይ ሊነግሩን የቻሉት ? ምን ያህል ነው የተናቅነው ? ምን ያህልስ ነው ግድ የማይሰጠን ? ኣረ እንደውም « ወያኔ በደለን » ብለን እለት እለት ከምናላዝነው ምን ያህሉ ነው የወያኔ ? በወያኔ መበደልን እንደ « ጎመን በጤና ኑሮ » የምናይ ሰዎች እንደው በምን ኣይነት ግንዛቤ ነው ስለ ሌላ ስርኣት በደል ልናወራ የምንችለው ? ወያኔን ተሸክሞ የኖረ ትከሻ እንዴት ምኒሊክን ለማዋረድ ተውረገረገ ? ወያኔን ኣምልኮ የሚኖር ህዝብ እንዴት የኣሉላ ዘር ነኝ ብሎ ሊፎክር ይችላል ? 10 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ ኣድገናል የሚል መሪ ከመሃከላችን እስኪገኝ የት ነበርን ? ኣክሱም ለወላይታው ምኑ ነው የሚል ባለጌ ባለ ራዕይ ተብሎ ሲሞካሽ ፥ በሃገር ላይ ሬሳ ሲሳለቅ እኛ የት ነበርን ? ኣዎ የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው!

Advertisements

Discussion

One thought on “የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው (ሄኖክ የሺጥላ )

  1. It is true,I myself admit my mistakes,I have been drinking,I was with no direction but now,I got Jesus and I began to thank him for my life,this is what this people need too,with out Christ people are blind,if you know what I mean.

    Like

    Posted by Tadesse | March 14, 2016, 12:19 pm

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Blog Stats

  • 52,481 hits
Advertisements
%d bloggers like this: