Uncategorized

የዘር ማጥፋት በኦጋዴን መሬት (በሳዲቅ አህመድ)

በሳዲቅ አህመድ

 • ሐሳባዊ እድገትና የዘር ማጥፋት

ፈጣን እድገት ታይቶባታል በምትባለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፈጣን የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ብቻ ሳይሆን የዘር ማጥፋትም እየተከናወነባት እንደሆነ መገለጽ ከጀመረ ቆይቷል።በተባበሩት መንግስታ የእድገት ሰንጠርዥ ዉስጥ ከ187 አገራት ዉስጥ 173ኛ የሆነችዋ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ በሆነ መመዘኛ ከበታች ካሉት እገራት የምትመደብ ናት።

Human rights abuse in Ethiopia's Ogaden region

ኢትዮጵያ በሰዎች የእድሜ እርዝመት፣በትምርትና በእለታዊ ገቢ አለም ላይ ካሉት አገራት ከመጨረሻዎቹ ተርታ  የምትመደብ ቢሆንም፤በምስራቅ አፍሪካ ዉስጥ ላለዉ የፖለቲካ፣የዲፕሎማሲ አጣብቂኝና የደህንነት ችግሮች ሲባል በህወሃት የሚመራዉ መንግስት ያልሆነዉን ሆኖ እንዲታይ ነጻ የሆነ የይለፍ ፍቃድን አግኝቷል በማለት ተንታኞች ያስረዳሉ።

ላለፉት 25 አመታት በኦጋዴን ዉስጥ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን በህወሃት የሚመራዉ መንግስት የጅምላ ግድያ፣የጅምላ እስር፣የአስገድዶ መድፈር ሰለባ መሆናቸዉ እምብዛም አለም አቀፋዊ ትኩረት ያላገኘ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ይታወቃል።

 • የኢትዮጵያ መንግስት የዘር ማጥፋት በዘጋቢ ፊልም ሲጋለጽ

መቀመጫዉን እንግሊዝ እገር ያደረገው The create trust በመባል የሚታወቀዉ የግብረሰናይ ተቋም “ኦጋዴን የኢቶጵያ ምስጢራዊ ሐፍረት” በሚል ርእስ ስር በሰራዉ አጭር ዘጋቢ ፊልም ላይ አነብ፣መርየም እና ፋጡማ የተባሉ ሶስት ሴቶች በኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት የደረሰባቸዉን ዘግናኝ መከራ አሳይቷል። የኦጋዴን ሴቶች በጫንቃቸዉ ላይ የተሸከሙት ስቃይና መከራ በከፊል በዘጋቢ ፊልሙ ቢገለጽም የሚደርስባቸዉ ጥቃት በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ከተገለጸው የላቀ እንደሚሆን የሚጠቁሙ መረጃዎች ሞልተዋል።

በምእራባዉያን አገራት ድጎማ እያገኘ ዜጎቹን የሚያሰቃየዉ ህወሃት መራሹ መንግስት በሚፈጥረዉ ሁከት ለጂኦ ፖለቲክሱ አስጊ ነዉ በማለት የሚገልጹ አሉ።በዚህም ሳቢያ የከፋ ነገር በአፍሪካ ቀንድ ላይ ከመፍጠሩ በፊት ለጋሾች እጃቸዉን ሰብሰብ ያደርጉ ዘንድ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አቤቱታ እያሰሙ ነዉ።

የአስገድዶ መደፈር ሰለባ የሆኑ እማኞችን ያናገረዉ The create trust በመባል የሚታወቀዉ የተራድኦ ተቋም የኢትዮጵያን መንግስት በድጎማ የሚጠግኑት አሜሪካ፣እንግሊዝና የአውሮፓዉ ህብረት እርዳታቸዉን እንዲመረምሩ ተጣርቷል።

አብዛኛዎቹ የአስገድዶ የመድፈርና የወሲብ ተጠቂዎች ስቃያቸዉን ለመናገር ፍቃደኛ  አይደሉም።የኢትዮጵያ መንግስት ከሚያደርስዉ ጥቃት እራሳቸዉን ለማዳን በእግር ወደ አጎራባች አገራት ይጓዛሉ።የህይወት መስዋእትነትን በመክፈል ኬንያ ስደተኛ ካምፕ የሚገቡ ቁጥራቸዉ በርካታ ነዉ።ከዚያም በላይ ዘግናኝ በሆነ መልኩ በጅልባዎች ተጭነዉ የመን የሚደርሱ አሉ።ከነዚህ መስዋእትነት ከተከፈለባቸዉ እልህ አስጨራሽ ጉዞዎች በኋላ አገር ሳሉ ኦጋዴን ዉስጥ የደረሰባቸዉን የሚናገሩት በጣም ጥቂቶቹ ናቸዉ።

 • የአነብ፣የመርየም እና የፋጡማ ዘግናኝ ስቃይ

መርየማ የተባለችው ሙስሊም የኦጋዴን ተወላጅ ድብደባ፣ግርፋት፣ አስገድ ከመደፈር ወሲባዊ ጥቃት አምልጣ ደደብ የስደተኛ መጠለያ ካምፕ ኬንያ መድረሷን ትናገራለች።መርየማ ኦጋዴን ዉስጥ እስር ቤት በቆየችባቸዉ ሁለት አመታት ዉስጥ ይደርስባት ስለነበረዉ ቶርቸር (የስቃይ) አያያዝ እንባዋን እያፈሰሰች ታስረዳለች። ሌላዉ ቀርቶ የሞተን ሰዉ አስክሬን ቀጥ አርጋ እስክትዝለፈለፍ ድረስ ተገዳ ትይዝ እንደነበር ትናግራለች።ሚጥሚጣ የተሞላበት ከረጢት በጭንቅላቷ እድሸከም ተደርጎ

ነፍሷን እስክስት ድረስ ተገዳ ት ሸከም እንደነበር በራሷ አንደበት አስረድታለች።

አንገቷ ላይ የገመድ ሸምቀቆ እስክትታነቅ ድረስ ታስሮ ነፍሷን በሳተችበት አስገዳጅ የወሲብ ጥቃት (አስገድዶ የመደፈር) ይደርስባት እንደነበር መርየማ በአንደበቷ ገልጻለች።

መርየማ በተደጋጋሚ አስገድዶ የመድፈር የወሲብ ጥቃት ስለባ መሆኗን እየገለጸች በስተመጨረሻም በተደጋጋሚ መደፈሩ የተለመደና ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ ሆነ ስትል እምባዋን እያፈሰሰች አስረድታለች።ብዙዎች አይነስዉር አካላ ጎዶሎ እንደሆኑ ያስረዳችዋ መርየማ የሰዉነት መንቀጥቀጥና የሚጥል በሽታ ሰለባ እንደሆነች ገልጻለች።እስር ቤት እንደገባሁ አንገቴ ላይ ሰንሰለት ታሰረ።በዚሁ መልክ እስር ቤት ዉስጥ ቀረሁ።ገና ከመያዜ በጎማ ዱላ ተደብድቤ ነበር።ጀርባዬን፣እጄን እና ትከሻዬን ተደብድቤያለሁ። እኔ ስያዝ አምስት ሴቶች አብረዉኝ ታስረዉ ነበር።እድሜዋ ትልቅ የሆነዉ አስራ ዘጠን ስጦን ትንሿ ደግም አስራ አመስት አመቷ ነበር።ስንያዝ ሴቶች በጣሙን በጦር ሰራዊት ሰደፍ በጣሙን ሲደበደቡ አይቼያለሁ።ሴቶቹ ልብሶቻቸዉ ተቀዳዶ ነበር።አንዳንደም እራፊ ጨርቅ ገላቸዉ ላይ ጣል ተደርጎ ይመለሱ እንደነበር አስታዉሳለሁ። ስትልም ሁናቴዉን በምሬት እዉስታለች።

ሌላኛዋተጠቂ አነብ ስትናገር  የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የጅምላ መቃብሮችን ለመሸፈን በጣሙን ይጥራል። ከሟቾች መካከል የገሚሱ አስክሬን የት እንደሚወሰድ እይታይም።ገሚሱ  በመጸዳጃ ቦይ (ትቦዎች) ላይ ይወረወራል በማለት በኦጋዴን ዉስጥ እየደረሰ ያለዉን የዘር ማጥፋት ወንጅል ገልጻለች።

የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ተጠቂ የሆነችዋ ፋጡማ ወታደሮቹ “እናንተ የኦጋዴን ተወላጆችን ሁላችሁንም እናጠፋችኋለን፣ማንኛዉንም የኦጋዴን ነዋሪ አንሻም፣ጥቃት እናደርስባችኋለን” በማለት ያደርጉት የነበረዉን ዛቻ ገልጻለች።

ዘጋቢ ፊልሙ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አስገድዶ በመድፈር የወሲብ ጥቃትን ያደርሳል፣ የወሲብ ባርነትን እንደ ቶርቸር (የስቃይ አያያዝ) ይጠቀማል፣ወታደራዊ ቅጥር ግቢዎችን ሴቶችን አስገድዶ በህብረት  በተደጋጋሚ ለመድፈርና ለወሲብ ባርነት ይጠቀማል ሲል የኢትዮጵያን መንግስት ይከሳል።

 • ኦጋዴን ኢትዮጵያዊ ሆኖ በህወሃት ጭቆና ስር መኖር

ከአምስት ሚሊዮን የኦጋዴን ነዋሪ መካከል 98% ሙስሊም ነዉ። ሶስት አራተኛዉ የሚሆነዉ የኦጋዴን ተወላጅ በቂ ዉሃና የጤና አገልግሎት አያገኝም።ህወሃት መራሹ መንግስት በኦጋዴን ህዝብ ላይ እያደረሰ ባለዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሳቢያ የኦጋዴን ኢትዮጵያዉያኑ ብሔራዊ ስሜት እየተሸረሸረ የመገንጠል ጥያቄ በአስገንጣዮቹ በኩል እያየለ መምጣቱ እየተገለጸ ነዉ።

በሺዎች የሚቆጠሩ በተደጋጋሚበሚያዙባት ኦጋዴን የብዙዎች ደብዛ ጠፍቷል። 1097 ሰዎች በታሰሩበት የስቃይ ካምፕ ዉስጥ ስንቶቹ ተርፈዉ እንደወጡ አይታወቅም።ኬንያ ደደብ ካምፕ የደረሱት በእምባ ጠፈጥፍ እየታጠቡ ያንን አሳቃቂ ህይወት በምልስት ይተርካሉ። መረጃን መሰብሰብ የሚፈልጉት የህወሃት መራሹ መንግስት እጋዚዎች ሴቶችን በማስገድድ መረጃን እንደሚሰበስቡ የስቃዩ ሰላባዎች ያስረዳሉ። መረጃ አልሰጥም ያለች ሴት ቅጣቷ ተገዶ በወሲብ መደፈር ነዉ። በአንድ ሰዉ ብቻ መደፈር የተለመደ ቢሆንም እስከፊዉ ቅጣት በቡድን እንዲት ሴት የምትደፈርበት ዘግናኝና ጸያፍ ተግባር ነዉ።ሴቶች እጅና እግራቸዉ ታስሮ  ይደፈራሉ። በርሃብ አለንጋ እየተገረፉ እስኪሞቱ ድረስ የሚቀጡ ብዙ ናቸዉ።ሌላዉን እስረኛ ለማሽበርና የዉሸት መረጃን ለማግኘት እስር ቤት ዉስጥ እንደ እንስሳ የሚታረዱም ነበሩ ሲሉ የህወሃት መራሹ መንግስት የስቃይ ሰለባዎች ያስረዳሉ።ሟቾች የመቀበር እድልን ሳይገኙ ቦይ ዉስጥ ይወረወራሉ።ሴት እስረኞች ባሉበት ክፍል ዉስጥ ብዙ የሞቱ ሰዎች አስክሬን ወታደሮቹ ያስቀምጣሉ።በእንባ ጠፈጠፍ እየራሱ የሚያስረዱት የኦጋዴን ተወላጆች “የነበረዉን ሁናቴ ማሰብም አይቻልም።ሟቾች አብዛኛዎቹ ወንድና ታዳጊ ወጣቶች ነበሩ።የሟቾች አስክሬን ከእስረኞቹ ጋር ለአራት ቀናት ይቀመጥና መንገድ ላይ ይጣላል።” ሲሉም ያንን መክእራና ስቃይ ዳግም ያስረዳሉ።

አብዛኛዎቹ የኦጋዴን ሴቶች የስቃይ አያያዝ (የቶቸር)የግርፋት፣የእስር፣ በወሲብ አስገድዶ የመድፈር፣ባልንና ልጅን የማጣት ሰለባ መሆናቸዉ ቀጥሏል። ይህ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በኢትዮጵይዉያን ዘንድ እምብዛም አትኩሮትን አላገኘም። ኢትዮጵያዉይን ሙስሊሞችም ለመብት የሚያደርጉት ትግል አለም የተደነቀበት ሆኖ አመስት አመት ቢዘልቅም፤ የኦጋዴን ወገኖቻቸዉን ስቃይና መከራ በማጉላቱ ረገድ ያላቸዉ ሚና እምብዛም የላቀ አለመሆኑ እየተስተዋለ ነዉ።

የኦጋዴን ሙስሊሞችን የማፈናቀልና ካገር እንዲሰደዱ የማድረጉ ዘመቻ ቀጥሏል። ኦጋዴን ዉስጥ ያሉት ዜጎች ተገደዉ ለህወሃት መራሹ መንግስት እንዲንበረከኩና የአምባገነናዊዉ መንግስት ሎሌ እንዲሆኑ እየተገደዱ ነዉ። በኦጋዴን ዉስጥ የነዳጅ ዘይት መገኘትና የምእራብ አገራት፣ራሽያ እና ቻይና የኦጋዴንን የነዳጅ ዘይት አንዱ አንዱን እየተጋፋ ለማዉጣት በተጣጣሩበት አያሌ አስርተ አመታት ንጹኋን የኦጋዴን ተወላጆች የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ሰለባ መሆናቸዉ ቀጥሏል።

አርሶ  አደሩና አርብቶ አደሩ የኦጋዴን ነዋሪ ተፈጥሮ የጋረጠችበትን ፈተና እያለፈ ለመኖር በሚያደርገዉ ትግል ላይ ተጨማሪ ኪሳራ ይዳረግበታል። ግመሎች፣ የቀንድ ከብቶች በኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሰራዊት ይዘረፋሉ። እዉቀት ከኦጋዴን ተወላጆች ላይ እንድትመክን ይደረጋል።ሆን ተብሎ ልጆች ትምርት ቤት ሔደዉ እዉቀትን እንዳይገበዩ ገና በለጋ እድሜ ይገደላሉ።ትምርት መማር የሚፈልግ ኢላማ ዉስጥ ይገባል፤ ከመማርና መሐይም ሆኖ ከመኖር አንዱን አንዲመርጥ ይገደዳል፤ ትምርቴን ብሎ የጸና መገደልም እጣ ፈንታዉ ሊሆን ይችላል።

 • የአፍሪካ ቀንድ ምስቅልቅልታና ግርግር

የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ነፍጥን መጨበጥና መዋጋት፣ የአልሸባብ የሽብር ተግባር መንሰራፋት፣ በሶማሊያ ዉስጥ ጠንካራ የሆነ ማእከላዊ መንግስት አለመኖሩ፣ በሶማሊያ የባህር ላይ ዘረፋ (piracy) መድራቱና የምስራቅና የምእራብ አገራት ጥቅም በዘረፋዉ በመነካቱ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ያሻዉን እንዲያደርግ ሁናቴዎች ተመቻችተዉለታል።ኦጋዴን በሶማሊያ፣በጅቡቲ፣በኬንያ እና በኢትዮጵያ መካከል ተከባ ደራሽ ሳይኖራት የጣረ-ሞት ማስተናገጃ ሆናለች። አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከንፈር ከምመጠጥ በስተቀረ ኦጋዴንን ሊታደግ እልቻለም። በኦጋዴን ዉስጥ ያለዉ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለማስቆም የጋራ ጥረት የሚያሻዉና ሰዎች ላቅ ባለ ድምጽ ተጠራርተዉ መፍትሔን የሚሻ ጉዳይ ቢሆንም ጥሪዉ የለሆሳስ ሆኗል።

 • ከፍተኛ የዘር ማጥፋት በኦጋዴን መሬት

በክፈለ ዘመናችን ላይ ይተገበራል ተብሎ የማይገመት የስቃይ አይነት በኦጋዴን ህዝብ ላይ ይፈጸማል። የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት በድንገት መንደርተኛን ሰብሰቦ ለመቀጣጫ የተወሰኑትን በጎረቤትና በቤተሰብ ፊት ይገድላል።የቀንድ ከብትን መዝረፍ ቤቶችን ማቃጠል የተለመደ ወንጀል እየሆነ ነዉ። በህወሃት የሚመሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለህጻን ለአዋቂዉ ደንታ ቢስ ናቸዉ።የሰባት ቀን አራስ የተደበደበችበት፣የሰባት ቀን አራስ ታፍና የተወሰደችበት ቦታ ቢኖር ኦጋዴን ነዉ ሲሉ የኦጋዴን ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ። አቅም ያልዉና አራሱን መከላከል የሚችለዉ ብቻ ሳይሆን አቅመ ደካሞች በጅምላ ግድያ የዘር ማጥፋት ሰለባ የሆኑባት ቦታ ናት ኦጋዴን።

ገና በንጋት በመቶች ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች መንደረሮችን ከበዉ ቤት ዉስጥ በመግባት የተኛዉን ሰዉ ወንድ ሴት ሳይሉ በጭካኔ ይደብድባሉ።የወታደሮቹ ሰደፍ ህጻን ሽማግሌ እይልም። ድሃዉ ህዝብ ንብረቱን ይዘራፈል። የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ በርሃብ እንዲሰቃይ ይደረጋል።ህዝቡ በዉጭ ተራድኦ ድርጅቶች የሚደረግለት የምግብ እርዳታ ይታገዳል። የእርሻ ሰብል ይወድማል።ቤቶች ይፈርሳሉ።በሺዎች የሚቆጠሩ ቤት አልባ ሆነዉ በየቦታዉ መበተናቸዉ ካልያም እገርን ለቀዉ መሰደዳቸዉ ይፋ መሆን ከጀመረ እመታት ተቆጥረዋል።

 • ልዩ ፖሊስ አገርን ሲያተራምስ

በበደል፣በጭቆናና በዘር ማጥፋት ወንጀል የስነልቦና ቀዉስ የደረሰባቸዉን ወጣቶች፣ስራ ፈትና መጥፎ ተግባራትን በማከናወን የሚታወቁ የኦጋዴን ተወላጆችን ህወሃት መራሹ ማእከላዊዉ መንግስት በመመልመል «ልዩ ፖሊስ» የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዉ ከጦር ሰራዊቱ ያልተናነሰ ጥቃት መሰንዘር ከጀመሩ ከስድስት አመት በላይ እንደሆነ የኦጋዴን ነዋሪዎች ያስረዳሉ።በየእስር ቤቱ የታጎሩ ሰዎችን ለማየት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተወካዮች  ሲመጡ የድሜ ባለጸጋዎቹን፣ ህጻናትን፣ሴቶችና አካለ-ስንኩላን ከእስር በእት ገለል እንዲሉ ይደርጋል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተወካዮች ሲመጡ ያለዉን የስቃይ ሁናቴ እስረኞቹ እንዳይናገሩ ዛቻ ይደርስባቸዋል። የእስር ቤት ጉብኝት ካለ ሁናቴዎችን ለመሸሸግ በጽዳት ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ይደረጋል።ጎብኚዎች ከሔዱ በኋላ ምክንያት ተፈልጎየሚገደልም እንደሚኖር ከሞት፣ከወሲባዊ ጥቃት የተረፉት እስረኞች አስረድተዋል።

 • አለምአቀፋዊ እይታ

በኦጋዴን ያሉ ኢትዮጵያዉን ህወሃት የሚያደርስባቸዉ ጥቃት የዘርም የሐይማኖትም ነዉ።ጥቃቱ ተመሳሳይና የቀጠለ ነዉ። ሁማን ራይትስ ዎች፣ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል እና ጄኖሳይድ ዎች የጦርነት ወንጀልና በንጹሃን ላይ የተፈጸመ አሳቃቂ ጥቃት በኦጋዴን ዉስጥ መቀጠሉን ገልጸዋል። ህወሃት መራሹ መንግስት መሰል ጥቃቶችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቦታዎች እየፈጸመ ከለጋሽ አገራት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላርን ይቀበላል። የተቀበለዉንም ገንዘብ ለዘር ማጥፋት መጠቀሙ በገሃድ የሚታይ ቢሆንም በወንጅሉ ተጠያቂ ሳይሆን ወንጅሎችን መፈጸሙን ቀጥሏል ይህ ነገር አልባት ሊያገኝ ይገባል፣ ለጋሽ አገራት ንጹሃን ዜጎን ማስፈጀታቸዉን ማቆም አለባቸዉ የሚል ክስ ቢሰማምም ሰሚ ጆሮን አላገኘም።

 • በሰዉ ልጆች ላይ የሚፈጸም ታላቅ ወንጀል

የኦጋዴን ተወላጆች ይገደላሉ።በጅምላ በሞት ይቀጣሉ።የዘር ማጥፋት

ይፈጸምባቸዋል።አንገታቸዉ በሰንሰለት ታስሮ ለቤተ ሙከራነት እንደቀረበ እንስሳ ይሆናሉ።ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ የሞት ቅጣትን ይቀምሳሉ።የግድያ ግብረሐይሎች ተሰማርተዉ የጅምላ ግድያን ያከናዉናሉ።ታፍነዉ የገቡበት እንዳይታወቅ ይደረጋል።ያለ አግባብና የፍርድ ቤት ትእዛዝ በማይታወቁ እስር ቤቶች እንዲማቅቁ ይደረጋል።ሴቶች የወሲብ ባርያ ይደረጋሉ።ወንዶች ተገደዉ በጉልበት ስራ እንዲሰማሩ ይደረጋል።የስቃይ አያያዝ ይያዛሉ፣ቶርቸር ይደረጋሉ።ህጻናት ገና ከማደጋቸዉ ተገደዉ በልዩ ፖሊስ ዉስጥ እንዲሰማሩ ይደረጋል።ሴቶች በጅምላ የአስገድዶ መድፈር ሰለባ ይሆናሉ። የኦጋዴን ተወላጆች የዘርና የሐይማኖት ጭቆና ይደርስባቸዋል። ቤት ቀዬአቸዉ ይቃጠላል። የቀንድ ከብት ይዘረፋል። እርሻ ይቃጠላል ወይም ይወድማል። ዘእጎች አገራቸዉን ጥለዉ እንዲሰደዱ ይደረጋል። ኦጋዴኖች ማንነታቸዉን እንዲሰረዝ የባህል እወካ ይደረግባቸዋል።ሐማኖታቸዉን እንዲቀይሩ የሌላ እምነት ሰባኪዎች እንዲያካብቧቸዉ ይደረጋል። እርስ በርስ እንዲጫረሱና ደም እንዲቃቡ ይደረጋል።

 • በመዝገበ ቃላት ላይ ያለ የወንጀል አይነት የሚፈጸምባት ቦታ

ኦጋዴን በመዝገበ ቃላት ሁሉ ያሉ የወንጀል አይነቶች እየተፈጸሙባት ነዉ። አለም አቀፍ ህጎች ሲጣሱ አለም ዝምታን መርጧል። አለምም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ወገን የኦጋዴን ተወላጆችን ካለባቸዉ መከራ ሊታደጋቸዉ ሲጥር እምብዛም አይታይም። ሌልዉ ቀርቶ የኦጋዴን ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያዉያን እጅግ የከፋ የሐይማኖት ጭቆና ሲደርስባቸው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ወገናቸዉ ጉዳያቸዉን ጉዳዬ ያለበት ሁናቴ በጉልህ አልታየም። ኢትዮጵያዊዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ለኦጋዴን ወገኑ ተግባራዊ እርዳታ ቀርቶ የጸሎት (የዱዓ) እርዳታ እያደረገ ነዉን? አጠያያቂ ነዉ።

ኦርጋዴን በመዝገበ ቃላት ላይ ሁሉ የሰፈሩ በሰዉ ልጅ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መናኸሪያ ሆናለች። ኢትዮጵያዉያኑ የሚጠበቅባቸዉ ሳያደርጉ ፈርንጅ ለኦጋዴን ህዝብ ለመድረስ ድንበር ጥሶ ይገባል። ወገኖቻችንን ከአሸባሪዉ ህወሃት  ለመታደግ ሰዉ እንጂ ፈረንጅ መሆን አይጠበቅብንም።የዚህ ፕሮግራም (ጽሁፍ) አቅራቢ እንኳ ኦጋዴንን አስመልክቶ አመርቂ ስራ ሳይሰራ ተቆርቋሪ ፈርንጅ ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ እንደቀሰቀሰዉ የሚካድ አይደለም። የኦጋዴን አስገንጣይ ሐይላት እንገንጠል ብለዉ የመንቀሳቀሳቸዉ እዉነታ የማይካድ ቢሆንም፤ ጭቆና የወለደዉን የመገንጠል ጥያቄ ሊያቆመዉ የሚችለዉ ፍቅር ነዉና ፍቅርን ለኦጋዴን ወገኖቻችን እንለግስ። ሁሌም ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

ዋቢ፦ Ogaden: Ethiopia’s hidden shame

Advertisements

Discussion

No comments yet.

Give a comment

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

facebook

https://www.facebook.com/

Blog Stats

 • 54,681 hits
Advertisements
%d bloggers like this: